በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዚደንት ጆ ባይደን የአሜሪካ የዛሬ ሁኔታ /ዘ ስቴት ኦፍ ዘ/ ዩኒየን ንግግር


የፕሬዚደንት ጆ ባይደን የአሜሪካ የዛሬ ሁኔታ /ዘ ስቴት ኦፍ ዘ/ ዩኒየን ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደን ጆ ባይደን ትናንት ሐሙስ ዘ ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን ተብሎ የሚጠራውን የአሜሪካ ወቅታዊ ሁኔታ መግለጫ ዓመታዊ ንግግር አድርገዋል። ባይደን የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ የተወካዮች ምክር ቤት እና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት በታደሙበት ጉባዔ ዓመታዊውን የሀገር ሁኔታ የሚዳስሰውን ንግግር ሲያደርጉ የትላንቱ ሦስተኛ ጊዜያቸው ነው።

በንግግራቸውም ለጋዛ ሰብአዊ ርዳታ ማስገባት እንዲቻል ትልቅ ዕቅድ ማውጣታቸውን አስታውቀዋል። ለዩክሬን የሩስያን ጥቃት ለመመከት የሚያስችላት ድጋፍ እንዲሰጣት ግፊት አድርገዋል። በኅዳር ወር በሚካሄደው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እንደሚፎካከሯቸው የሚጠበቁት ዶናልድ ትረምፕ "ለሀገራችን አደጋ ናቸው" በማለት አስጠንቅቀዋል። የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ ፕሬዚደንታዊ ምርጫው እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት ትልቅ ትኩረት የሚስበውን ንግግር የዳሰሰ ሪፖርት አጠናቅራለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG