በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት የጅምላ ግድያን የሚያስቀርበትን መንገድ እየመከረ ነው


የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ ሻክ ሹመር
የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ ሻክ ሹመር

የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጭዎች በአገሪቱ ታሪክ እጅግ ከከፉት ሁለተኛው የሆነውን የቴክሳሱ የትምህር ቤት ግድያን ተከትሎ፣ ከመሳሪያ ሽያጭ በፊት፣ ጥብቅ የኋላ ታሪክ ምርመራ እንዲካሄድ በሚያዘው ህግ ላይ፣ ዛሬ ሀሙስ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተነገሯል፡፡

ግድያው በመላ አገሪቱ ያለውን የመሳሪያ ቁጥጥር ክርክር ዳግመኛ የቀሰቀሰ ሲሆን በፖለቲከኞች ዘንድ ህግ ሆኖ የማለፉ ዕድል እጅግ ጠባብ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ ዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ ትምህርት ቤት አንድ አጥቂ በከፈተው ተኩስ 19 ህጻናትና ሁለት ሰዎችን ጨምሮ 21 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ግድያውን አስመልክቶ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ባይደን “እንደው ስለ እግዚአብሄር ሙሉ ለሙሉ ማቆም ባያስችለን እንኳ፣ የእልቂቱን መጠን ከመሰረቱ ለመቀነስ ማድረግ ያለብንን የምናደርገው መች ነው?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ህጉን ከሚቃወሙት መካከል የቴክሳሱ ገዥ ግሬግ አቦት የ18 ዓመቱ ወጣት ግድያውን ከመፈጸሙ በፊት ምንም ምልክት አለመስጠትን ገልጸዋል፡፡ ኦቦት ጥብቅ የመሳሪያ ቁጥጥርን ከመጠየቅ ለአእምሮ ጤና አገልግሎት ድጋፍ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አያይዘውም በሰጡት አስተያየት

“ይህን ስል ያሳፍረኛል፣ በቴክሳክስ ባሉ ትምህርት ቤቶች ይልቅ በየሳምንቱ ብዙ ሰዎች የሚሞቱት ቺካጎ ውስጥ ነው፣ ጥብቅ የመሳሪያ ቁጥጥር ህግ አውጥተን ተግባራዊ ብናደርግ ይህንን ችግር ይፈታዋል ብሉ የሚያስቡ ሰዎች ምናልባት ያንንን እንዲገነዘቡ ያስፈልገናል፣ ቺካጎ ሎስ አንጀለስና ኒው ዮርክ ያንን አያረጋግጡም፡፡” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዴሞክራቶች እጅግ በጠበበች የበላይነት ድምጽ የሚቆጣጠሩት ምክር ቤት ውሳኔዎቹን እንዲያሳልፍ አሳስበዋል፡፡

ዴሞክራቱ የህግ መወሰኛው ምክር ቤት መሪ ሻክ ሹመር፣

“የአሜሪካ የመሳሪያ ወረረሽኝ በአምሳያችን ካሉ የትኞቹም አገሮች የሚወዳደር አይደለም፡፡ አንድም አሜሪካዊ ከዚህ ስጋት ነጻ አይደለም፣ አሜሪካውያን እጅግ በጣም ታመውበታል እጅግ ታክቷቸዋል፡፡” ብለዋል፡፡

እኤአ በ2021 ፒው የህዝብ አስተያየት ድምጽ መሰብሰቢያ ባወጣው መረጃ ግማሽ የሚሆኑት አሜሪካውያን የመሳሪያ ጥቃትን እንደ ትልቅ ችግር አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ሁለቱም ዴሞክራትና ሪፐብሊካን በግልም ሆነ በመሳሪያ ገበያዎች ለሚሸጡ መሳሪያዎች የኋላ ታሪኮች አስቀድመው ይመርመሩ የሚለውን የሚፈልጉት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጥብቅ ቁጥጥር ይደረግ በሚለው ዙሪያ በርካታ ተቃዋሞዎች ለዓመታት የተካሄዱ ቢሆንም አንዳቸውም ቢሆኑ ምክር ቤቱ ህጉን እንዲያሳልፍ ማድረግ አለመቻላቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG