በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት 2016 አከባበር በዓለም ዙርያ


የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት 2016 አከባበር በዓለም ዙርያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:43 0:00

የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት 2016 አከባበር በዓለም ዙርያ

በህዝባዊ የበዓል ዝግጅቶች ላይ ጥቃት ሊደርስ ይችላል የሚል ዛቻ ባስከተለው ስጋት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች በአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ክብረ በዓል ጥብቅ የጸጥታ ጥበቃ እየተካሄደ ነው።

2016ን በቀዳሚነት ከተቀበሉት ከተሞች አንዱዋ በሆነችው በሲድኒ አውስትሬሊያ በአምስት ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለአስራ ሁለት ደቂቃ በዘለቀ ግዙፍ ርችት ህዝቡ በዓሉን አክብሯል።

በሩሲያ ደግሞ ባለስልጣናቱ ታሪካዊውን ወትሮ የአዲስ ዓመት በዓል የሚካሄድበትን ቀዩን አደባባይ ዘግተውታል። ስለርምጃው የሰጡት መግለጫ አይኑር እንጂ ባለፈው ጥቅምት ወር ግብጽ ውስጥ ከወደቀው የሩስያ መንገደኛ አውሮፕላንና ሶሪያ ውስጥ ከቀጠለችው የቦምብ ጥቃት በተዛመደ የሽብር ተግባር ስጋት ምክንያት ይመስላል።

ኢንዶኔዥያ ጃካርታ ውስጥም ባለስልጣናት የሽብር ጥቃት ሴራ መኖሩን ስለደረሱበት ከተማዋ በክፍተኛ ጥበቃ ላይ ነች።

በቤልጂየም የዋና ከተማዋ ብረሰልስ የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል በሽብር ስጋት ምክንያት ተሰርዙዋል። የከተማዋ ከንቲባ የርችት ትርኢት ለመመልከት የሚወጣውን ብዙ ሺህ ህዝብ ለመፈተሽ እንደማይቻል ባለሟይዎች ስለደመደሙ መሆኑን ገልጸዋል።

የፍረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስም ርችት ትርዒት ሰርዛለች ሌላውንም ክብረ በአል ጋብ አድርጋለች።

ዩናይትድ ስቴትስት ደግሞ ኒው ዮርክ ከተማ ጠብመንጃ እና ሌሎችም የጨረር መከታተታያዎችና አነፍናፊ ውሻዎችን የያዙ በሺዎች የተቆጠሩ ፖሊሶችን አሰልፋ በየዓመቱ ለሚደረገው ለታይምስ ስኩዌር አደባባይ ለአዲስ ዓመት በአል ተዘጋጅታለች። ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል። ባለልስጣናት የሚሰነዘር የጥቃት ዛቻ ቢኖር በማለት ከውጭና ወደውጭ የሚደረጉ ግንኙነቶች ኮሙኒኬሽኖችን እየተታተሉ ናቸው።

ፖሊሶችና የፌደራሉ ምርመራ ቢሮ በኒው ዮርኩም ሆነ በሌሎች ከተሞች ክብረበዓል ላይ በግልጽ የተሰነዘረ የሚታመን ዛቻ እንደሌለ ኣመልክትዋል። ሆኖም ከፓሪሱና ከካሊፎርኒያ ሳንበርናርዲኖ ከደረሱት የሽብር ጥቃቶች በሁዋላ ለማንኛውም በንቃት እንከታታላለን ብለዋል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአውሮፓውያን አዲስ ዓመት 2016 አከባበር በዓለም ዙርያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:47 0:00

በኒው ዮርክ የነበረውን አከባበር እንዲሁም ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

አዲስ ዓመት 2016 በኒው ዮርክ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:34 0:00

የፎቶ መድብሎቻችንንም ይመልከቱ። መልካም አዲስ ዓመት ከቪኦኤ!

XS
SM
MD
LG