የአውሮፓውያን ኣዲሱ ዓመት 2016 አርብ እለት አሃዱ ብሉዋል።
ሃሙስ ማታ በዋዜማው በኒው ዮርኩ የታይምስ ስኩዌር አደባባይ በተካሄደው ክብረ በዓል ቁጥሩ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ 2016 የሚል የተጻፈበት መነጽር እና ሃምራዊ ቀለም ያላቸው ባርኔጣዎች አድርጎ አዲሱን ዓመት ተቀብሏል።
2016 የሚል የተጻፈበት መነጽር
ልክ እኩለ ሌሊት ላይ በከተማዋ ሰማይ ግዙፉዋ ኣንጸባራቂ ክሪስታል ኩዋስ ቦግ ከማለቱ በፊት ሀመኑን ስግግር ከማብሰሩዋ በፊት እንግሊዛዊ ድምጻዊ ጄሲ ጄ የጆን ሌነንን ኢማጅን "Imagine"ታዋቂ ዜማ ኣስመታለች።
የወረቀት ጌጦች ኮንፌቲዎች ተለቀቁ ከአሜርካ የአዲስ ዓመት ክብረ በዓል ትልቁ በሆነው በታይምስ አደባባዩ ፈንጠዚያ የርችት ተኩስ የኒውዮርክ ሰማያት ተግ ብሎ አድምቋል። የፍራንክ ሴናትራ "ኒውዮርክ ኒውዮርክ" የሬይ ቻርልስ "አሜሪካ" እና የሉዊስ አርምስምትሮንግ "ዎንደርፉል ዎርልድ" የተሰኙ ዘፈኖችም ተሰብሳቢውን አስደስተዋል።
የኒው ዮርክ ባለስልጣናት ለክብረ በዓሉ የጸጥታ ጥበቃ ስድስት ሺህ መለዮ የለበሱ፣ ነጭ ለባሽና ፈረሰኛ ሃይሎችን አሰማርተዋል አንዳችም የተፈጠረ ችግር አልተዘገበም።
የዩናይትድ ስቴይትስ ባለስልጣናት ከውጭ አካላት ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን በንቃት ሲከታተሉ መቆየታቸውን አስታውቀዋል። የዜና ዘገባችንን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።