በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ሪፑብሊክ የተካሄደው ምርጫ በጥልቅ እሳዝኖናል ሲል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

ፋይል ፎቶ - የኮንጎ ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት ዴኒስ ሳሱ ኒጉዌሶ እ.አ.አ. 2015
ፋይል ፎቶ - የኮንጎ ሪፑብሊክ ፕሬዚደንት ዴኒስ ሳሱ ኒጉዌሶ እ.አ.አ. 2015

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ባወጡት መግለጫ በምርጫው ሂደት በስፋት የተዘባ አሰራር እንደታየበት ጠቅሰው የድምጽ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ በኋላ የተቃዋሚ ደጋፊዎች መታሰራቸው ሂደቱን አጉድፎታል ብለዋል።

በኮንጎ ሪፑብሊክ የተካሄደውና የፕሬዚደንት ዴኒስ ሳሱ ኒጉዌሶን የስልጣን ዘመን እንዲራዘም ያደረገው ምርጫ በጥልቅ እሳዝኖናል ሲል የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ባወጡት መግለጫ በምርጫው ሂደት በስፋት የተዘባ አሰራር እንደታየበት ጠቅሰው የድምጽ አሰጣጡ በሰላማዊ መንገድ ተጀምሮ በኋላ የተቃዋሚ ደጋፊዎች መታሰራቸው ሂደቱን አጉድፎታል ብለዋል።

በኮንጎዋ ዋና ከተማ ብራዛቪል ሰኞ ዕለት ንጋት ላይ ነዋሪዎች በተኩስ እና በፍንዳታ ድምጽ በርግገው ከቤታቸው የተሰደዱት በሺዎች የተቆጠሩ ነዋሪዎች ሁኔታ ዩናይትድ ስቴትስን በጥልቅ እንዳሳሰበ ተናግሯል።

የኮንጎ መንግስት ስለድንገቱ ሲናገር ትጥቁን እንዲፈታ የተደረገ ሚሊሺያ አባላት የነበሩ ሰዎች በመንግስት ዒላማዎች ላይ ጥቃት አድርሰው ሶስት የጸጥታ አባላትንና ሁለት ሰላማዊ ሰዎች መግደላቸውን ተናግሯል። ከአጥቂዎቹ ደግሞ አስራ ሁለቱን ገድለናል ሲል አስታውቋል።

በምርጫው የተወዳደሩ ተቃዋሚ ዕጩዎች ሂደቱ ለፕሬዚደንት ኒጉዌሶ ያደላ ነበር በማለት አማርረዋል። ከተቃዋሚ ዕጩዎች እንዱ የሆኑት ጄኔራል ዣን ማሪ ሞኮኮ ህዝቡ የምርጫውን ውጤት እንደሚቃወም በህዝባዊ ዕምቢተኝነት ርምጃ እንዲያሳይ አሳስበዋል።

በምርጫው ሁለተኛ የሆኑት ዕጩ ጊ ብራይስ ኮሌላስ በበኩላቸው ምርጫው ፍትሃዊ አልነበረም፣ ሆኖም ሁከት እንዳይቀሰቀስ ለመከላከል ስል ውጤቱን እቀበላለሁ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG