ዋሽንግተን ዲሲ —
በኮንጎ ሪፑብሊክ መዲና ብራዛቪል ትላንት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ሶስት ፖሊሶችና ሁለት ታጣቂዎች እንደተገደሉ ተዘግቧል።
ውጊያው የተከፈተው የሀገሪቱ ፕረዚዳንት ዴኒስ ሳስዋ ንጉዌሶ በአጨቃጫቂ ምርጫ ለሶስተኛ ጊዜ ካሸነፉ ባኋላ ነው።
ፖሊሶች እንደሚሉት “ኒንጃዎች” የተባለው ጸረ ንጉሶ ሚልሻ የቀድሞ አባላት በአከባቢው የፖሊስ ጣብያ፣ በወታደራዊና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ወረራ አካሄደው በእሳት አጋይተዋቸዋል።