በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ ሪፑብሊክ መዲና ፖሊሶች ማንነታቸው ካልተወቀ ታጣቂዎች ጋር ተኩስ ተለዋውጠዋል


የኮንጎ ካርታ
የኮንጎ ካርታ

በደቡባዊ ብራዛቪል በሚገኙ ባኮንጎና ማኬሌኬ በተባሉ መንደሮች ከሌሊቱ 9 ሰአት ላይ የጀመረው ተኩስ እስከንጋቱ እንደቀጠለ ተዘግቧል።

የኮንጎ ሪፑብሊክ መዲና ፖሊሶች ማንነታቸው ካልተወቀ ታጣቂዎች ጋር ተኩስ ተለዋውጠዋል።

ፕረዚዳንት ዴኒስ ሳስዋ ንጉሶ እንደገና ከተመረጡ ወዲህ የመጀመርያ አብይ ግጭት መሆኑ ነው። በደቡባዊ ብራዛቪል (Brazzaville) በሚገኙ ባኮንጎና ማኬሌኬ በተባሉ መንደሮች ከሌሊቱ 9 ሰአት ላይ የጀመረው ተኩስ እስከንጋቱ እንደቀጠለ ተዘግቧል።

ኒንጃ "Ninja" የተባሉ ባለፈው ወር በተካሄደው ፕረዚዳንታዊ ምርጫ የተሸነፉ ተወዳዳሪ አባት ታማኝ የነበሩ ሚሊሻዎች ማያንጋ በተባለው ወታደራዊ ሰፈር ላይ ጥቃት ከፍተው እሳት እንደለኮሱበት፣ በአራት የፖሊስ ጣብያዎችና በከንቲባው ጽህፈት ቤት ላይም ጥቃት እንደከፈቱ የመንግስት መግለጫ ጠቁሟል። ስለደረሰ ጉዳት የተገለጸ አነገ የለም።

ጥቃቱ ለፕረዚዳንትነት ተወዳድረው ከነበሩት ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት ይኖረው እንደሆነ ማረጋገጫ እንደሌለውና ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን መንግስት ጠቁሟል። ንጎሶ እንደገና የተመረጡት የስልጣን የጊዜና የእድሜ ገደብ ከህገ-መንግስቱ እንዲነሳ በህዝብ ድምጽ ከተደገፈ በኋላ ነው።

XS
SM
MD
LG