በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶሪያ ውስጥ አስራ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን የተባበሩት መግሥታት ድርጅት አስታወቀ


ፋይል ፎቶ - ሶርያውያን ከስድስት ወራት በኃላ የሚመጣላቸውን ርዳታ እየጠበቁ (አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ፎቶ/ AFP)
ፋይል ፎቶ - ሶርያውያን ከስድስት ወራት በኃላ የሚመጣላቸውን ርዳታ እየጠበቁ (አጃንስ ፍራንስ ፕረስ ፎቶ/ AFP)

ሶሪያ ውስጥ አስራ ሶስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን የተባበሩት መግሥታት ድርጅት ማስታወቁን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ሁኔታው በጥልቅ ያሳሰባት መሆኑን አስታውቃለች።

በመንግሥታቱ ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር በተለይ በሰራዊት በተከበቡ አስራ አምስት የሶሪያ አካባቢዎች ስላለው ሁኔታ አትኩረው ተናግረዋል።

​ለአስራ ሁለቱ አካባቢዎች መግቢያ መውጫ ማጣት ጠጠያቂው የሶሪያ መንግሥት ነው ያሉት ሳምንታ ፓወር ካለፈው ታህሳስ ወር መጀመሪያ ወዲህ ቢያንስ ሰላሳ አምስት ሰዎች መሞታቸውን አመልክተዋል።

የሶርያ ካርታ
የሶርያ ካርታ

የሀገሪቱ ሁሉም ወገኖች የሰብዓዊ ረድዔት ቡድኖች ያለአንዳች ዕንቅፋት ኣንዲገቡ ፈቃድ እንዲሰጡ እምባሰድር ፓወር ተማጽነዋል።

XS
SM
MD
LG