በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እ.አ.አ. በ2016 ዓ.ም ሜዲቴራኒያን ባህርን ሊያቋርጡ ሲሞክሩ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ2500 በልጧል


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ዊልያም ስፒንድለር (William Spindler) በአጠቃላይ በሜደቴራኒያን ባህር በአሁኑ ጊዜ ባህሩን ለማቋረጥ ከሚሞክሩ ሰዎች ከሰማኒያ አንድ ሰው አንዱ ህይወቱን ባህሩ ላይ የመቀረት ዕጣ ሊገጥመው እንደሚችል ገልጿል።

በዚህ በያዝነው የአውሮፓውያን 2016 ዓመተ ምህረት እስካሁን ባለው ጊዜ አውሮፓ ለመግባት ሜዲቴራኒያን ባህርን ሊያቋርጡ ሲሞክሩ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከ2500 በልጧል።

ለማነጻጸር፣ ባለፈው 2015 በመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት የሞቱት ቁጥር 1855 እንደነበር ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ዊልያም ስፒንድለር (William Spindler) በአጠቃላይ በሜደቴራኒያን ባህር በአሁኑ ጊዜ ባህሩን ለማቋረጥ ከሚሞክሩ ሰዎች ከሰማኒያ አንድ ሰው አንዱ ህይወቱን ባህሩ ላይ የመቀረት ዕጣ ሊገጥመው እንደሚችል ገልጿል።

የአሜሪካ ድምጽ የፍልሰተኞችና ስደተኞች ጉዞን በዝርዝር የሚዳስስ "ከርታታ ሥውሩ የአፍሪካ ዳያስፖራ" የተሰኘ ዘገባ አዘጋጅቷል። ፋይሉን በመጫን ይጎብኙ።

ከሰሜን አፍሪካ ወደ ጣሊያን የሚወስደው የባህሩ መስመር የባሰ አደገኛ መሆኑን በዚህ ዓመት ከሞቱት መካከል 2119ኙ በዚህ መስመር ለማቋረጥ የሞከሩ መሆናቸውን አክለዋል። በዚያ መስመር ከሃያ ሶስት ሰው አንዱ የመስጠም ዕጣ ሊገጥመው እንደሚችል ተጠቁሟል።

በዚህ መስመር የሚጓዙት አብዛኞቹ ፍልሰተኞች ናይጄሪያውያንና ጋምቢያውያን ሲሆኑ በቱርክና ግሪክ መስመር ደግሞ የሚበዙት ሶሪያውያን ፡ ኣፍጋኖች፡ እና ኢራቃውያን መሆናቸውን የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት ብቻ ቁጥራቸው ስምንት መቶ ሰማኒያ የሚገመት ፍልሰተኞችና ስደተኞች ባህሩን ለማቋረጥ ሲሞክሩ አልቀዋል።

ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:43 0:00

XS
SM
MD
LG