በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንግሊዝ 'የተበላሸውን' የብሬግዚት ስምምነት ማሻሻል እንደምትችል አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ


አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር መግለጫ እየሰጡ እአአ ሃምሌ 6/2024
አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር መግለጫ እየሰጡ እአአ ሃምሌ 6/2024

አዲሱ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር፤ እንግሊዝ ከአውሮፓ ኅብረት እንድትሰናበት ካደረገው ብሬግዚት በኋላ፣ ከህብረቱ ጋር በተደረገው የንግድ ልውውጥ ሕጎች ዙሪያ የተሻለ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና "የተባላሸ" ሲሉ የገለጹትን በቀድሞ ፕሬዝዳንት ቦርስ ጆንሰን የተፈረመ ውል ለማሻሻል ሰኞ እለት ቃል ገብተዋል።

ስታርመር፣ ከሰሜን አየርላንድ መሪዎች ጋር በዋና ከተማዋ ቤልፋስት ከተነጋገሩ በኃላ ባደረጉት ንግግር አዲሱ መንግስታቸው ከአውሮፓ ህብረት ጋር መተማመን ለመፍጠር፣ መጀመሪያ አሁን ባለው ስምምነት መሠረት ለውጦችን ማድረግ እንደሚኖርበት አመልክተዋል።

ባለፈው ሳምንት በከፍተኛ ልዩነት ተፎካካሪያቸውን በልጠው ያሸነፉት ስታርመር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል "ቦሪስ ጆንሰን ካመጡብን የተበላሸ ስምምነት የተሻለ ስምምነት ማግኘት እንችላለን፣ በዚህ ላይም እንሰራለን" ያሉ ሲሆን የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር ግን አሁን ለተደረጉት ስምምነቶች ቁርጠኝነታችንን ማሳየት አለብን ብለዋል።

ሌበር ፓርቲ ያለተገደበ የሸቀጦች፣ አገልግሎቶች እና የሰዎች እንቅስቃሴ የሚደረግበትን የአውሮፓ ህብረት ገበያ እንደማይቀላቀል ቢያስታውቅም፣ እ.አ.አ በ2010 እንግሊዝ ጥላ ከወጣችው ከ27ቱ ሀገራት ጥምረት ጋር ያሉትን አንዳንድ የንግድ መሰናክሎች ግን ማስወገድ እንደሚቻል ገልጿል።

በሰሜን አየርላንድ ትልቁ የእንግሊዝ ደጋፊ የሆነው ፓርቲ ፤ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በንግድ ልውውጦች ዙሪያ ጥቂት በየካቲት ወር ማሻሻያዎችን ካደረጉ በኃላ፣ የተለያየ ውሳኔ የመስጠት አቅም ላለው ጉባዔ ተገዢ ላለመሆን አሳልፈውት የነበረውን ውሳኔ ሽረዋል።

በአየርላንድ ብሔርተኛው ሲን ፌይን በፓርላማ አብልጫ ድምፅ ያለው ሆኖ መመረጡን ተከትሎ በአየርላንድ ህዝበ ውሳኔ ሊካሄድ በሚችልበት ሁኔታ ላይ የተጠየቁት ስታርመር፣ ለሦስት አስርት አመታት የዘለቀውን ብጥብጥ ያስቆመው እና አየር ላንድ እራሱን እንዲያስተዳድር ላስቻለው "የጉድ ፍራይዴስ ስምምነት" ተገዢ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

እሁድ እለት የስኮትላንድን ዋና ከተማ ኤደንብራ የጎበኙት ስታርመር፣ ከምርጫ በኃላ በአራቱም የእንግሊዝ ግዛቶች እያደረጉ ያሉትን ጉብኝት ቀጥለው ሰኞ እለት በዌልስ ዋና ከተማ ካርዲፍ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG