በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእንግሊዝ ምርጫ ነገ ይካሄዳል


ፋይል፦ ነዋሪዎች ድምጻቸውን የት እንደሚሰጡ የሚጠቁም ምልክት ለንደን፣ እ አአ ግንቦት 3/2024
ፋይል፦ ነዋሪዎች ድምጻቸውን የት እንደሚሰጡ የሚጠቁም ምልክት ለንደን፣ እ አአ ግንቦት 3/2024

በእንግሊዝ ምርጫ ነገ ሐሙስ ሲካሄድ፣ ላለፉት 20 ወራት በሥልጣን ላይ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ በወንበራቸው ላይ መቆየት መቻላቸው የሚወሰንበት እንደሚሆን ተነግሯል።

ድምፅ ሰጪዎች ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሠራተኛ ፓርቲው ድምፅ እንደሚሰጡ በስፋት በመጠበቅ ላይ ቢሆንም፣ የወግ አጥቂ ፓርቲው ሱናክ በበኩላቸው የምርጫውን ውጤት ከወዲሁ መወስን እንደማይቻል ሲያሳውቁ ቆይተዋል።

በሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች መሪነቱን የያዘው የሠራተኛ ፓርቲውም፣ በድምፅ ሰጪዎች ዘንድ እናሸንፋለን የሚል መዘናጋት እንዳይኖር አስስቧል።

በመላ ሃገሪቱ ድምፅ ሰጪዎች ለውጥ ቢሹም፣ ነገር ግን የሚጠብቁት ለውጥ ይመጣል ብለው በተስፋ እንደማይጠብቁ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG