በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእንግሊዙ ምርጫ ሌበር ፓርቲ እንደሚያሸንፍ ይጠበቃል


ፋይል፦ ነዋሪዎች ድምጻቸውን የት እንደሚሰጡ የሚጠቁም ምልክት ለንደን፣ እአአ ግንቦት 3/2024
ፋይል፦ ነዋሪዎች ድምጻቸውን የት እንደሚሰጡ የሚጠቁም ምልክት ለንደን፣ እአአ ግንቦት 3/2024

የብሪታኒያ ሕዝብ በዛሬው ዕለት በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ድምጹን ሲሰጥ ውሏል፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሪሺ ሱናክ እና ባለቤታቸው በበፊቱ መኖሪያቸው በኖርዝ ዮርክሻይር ድምጻቸውን ሰጥተዋል፡፡ በዚህ ምርጫ ላለፉት 14 ዓመታት ስልጣን ላይ የቆየው የሳቸው ወግ አጥባቂ ፓርቲ ስልጣን ሳይነጠቅ እንደማይቀር እየተነገረ ነው፡፡

ሀገሪቱ ምጣኔ ሐብቷ በተዳከመበት፡ እና ህዝቡ በተቋማት ላይ ያለው አመኔታ እየተሸረሸረ በሄደበት እና ማህበራዊ መስተጋብሩም ላይ ውጥረት በሚታይበት በዚህ ወቅት በሚደረገው ምክር ቤታዊ ምርጫ አዲሱን አስተዳደሩን የሚመርጠው የብሪታኒያ ሕዝብ ሌበር ፓርቲውን ወደስልጣን ያመጣል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል፡፡

የምርጫ አሰጣጡ ሂደት ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን የተለያዩ የዜና ማሰራጫዎች የትኛው ፓርቲ የተሻለ ውጤት እንዳመጣ ተቀራራቢ ምስል የሚሰጠውን የምርጫ ውጤት ያሳውቃሉ። ከሀገሪቱ 650 ክልሎች ከሚሰበሰበው ድምፅ 362 የፓርላማ መቀመጫዎችን የሚያገኘውፓርቲ አሸናፊ ሆኖ አርብ ጠዋት ይፋ ይደረጋል።

ከሕዝብ የተሰበሰቡ አስተያየቶች እንደሚጠቁሙት መራጮች ከ14 ዓመታት የተመሰቃቀለ አገዛዝ በኃላ፣ ወግ አጥባቂ ፓርቲውን እና በስልጣን ላይ ያሉ የመንግስት ሚኒስትሮቹን ያባርራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG