በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ጥሪ አቀረበች


በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ጥሪ አቀረበች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:52 0:00

በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶች በውይይት እንዲፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ዳግም ጥሪ አቀረበች

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ፣ “የፖለቲካ ውይይት ለኢትዮጵያ ሰላም ብቸኛው መፍትሔ ነው” ሲሉ ዳግም አሳስበዋል።

በቅርቡ በዝቋላ ገዳም መነኰሳት አባቶች ላይ የተፈጸመውን ግድያም አምባሳደሩ አውግዘዋል። በግጭቶች መቀጠልና በሲቪሎች ግድያ አሳሳቢነት ላይ የተለያዩ አካላት የሚያወጡት መግለጫ ትኩረት እያጣ እንደኾነ የገለጹት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ዲሬክተር መስዑድ ገበየሁ፣ በጉዳዩ ላይ ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ ለማድረግ የታቀደው አገራዊ ምክክርም፣ በማያባሩ ግጭቶች እየተፈተነ እንደኾነ የገለጹት የምክክር ኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ፣ በግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን ለማነጋገር ጥረት እየተደረገ እንደኾነ ገልጸዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG