በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዝቋላ ገዳማውያንን በገደሉ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው - የኦሮሚያ ክልል


የዝቋላ ገዳማውያንን በገደሉ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው - የኦሮሚያ ክልል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00

የዝቋላ ገዳማውያንን በገደሉ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ እየተወሰደ ነው - የኦሮሚያ ክልል

ከዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም አራት መነኰሳት አባቶችን አግተው በመውሰድ ግድያ ፈጽመዋል ባላቸው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ላይ ርምጃ እየወሰደ እንደሆነ፣ የኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ አስታውቋል።

በየደረጃው ያሉ የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በተቀናጀ ኹኔታ “ሸኔ” ሲል በጠራቸው የታጣቂው ኀይሎች ላይ ርምጃ እየወሰዱ እንደሚገኙ ቢሮው ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

“ኦነግ ሸኔ በተባለው ታጣቂ ቡድን ተገደሉ” ያላቸውን አራት የገዳሙን አባቶች በስም የጠቀሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ፣ የፌዴራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት፣ ገዳማውያኑንና ገዳሙን የመታደግ ሥራ እንዲሠሩ ጠይቋል።

በግድያው የተወነጀለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ዓለም አቀፍ ቃል አቀባይ ኦዳ ተርቢ ድርጊቱን አስተባብለዋል። የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገረው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ሁኔታውን በምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG