ዋሽንግተን ዲሲ —
የቱኒዝያ ወታደሮች፣ ከሊብያ ጋር በሚዋሰነው ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ አንድ የፓሊስ ጣቢያና አንድ የጦር ካምፕ ላይ ጥቃት ያካሄዱ 21 ነውጠኞችን እንደገደሉ፣ የቱኒዝያ አገር ውስጥ ሚኒስቴር ዛሬ ሰኞ አስታወቀ።
ግጭቱ የተካሄደው በን ጉዌራንዴ በተሰኘችው ደቡባዊ-ምሥራቅ ከተማ ውስጥ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት ቢያንስ አራት ሲቪሎችና አንድ ወታደር መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
የተኩስ ልውውጡ እንደጀመረ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤቶቻቸው እንዳይወጡም ባለሥልጣንቱ አሳስበዋል። ሊብያ ውስጥ፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለውን በድን ጨምሮ አማጽያን
በመበራከታቸው፣ የቱኒዝያ ኃይሎች በምዕራባውያን ወታደሮች እየታገዙ እንደሆነም ይታወቃል። አጭር የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።