በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የዓለማችን ዓይን ያነጣጠረው በቱኒዝያ ላይ ነው" ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ


"የዓለማችን ዓይን ያነጣጠረው በቱኒዝያ ላይ ነው፥ ለአረብ መነሳሳት እንደ እምብርት የምትቆጠረው ሀገር ስኬታማ እንድትሆን ደግሞ የአሜሪካ ፍላጎት ነው” ሲሉ ዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ( John Kerry) ተናገሩ።

ዩናይትድ ስቴትስ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry) ይህን አስተያየት ዛሬ ከቱኒዝያ የሰጡት፥ በሦሪያ የፖለቲካና ፀጥታ አለመረጋጋት ላይ ያተኮረ የሦስት አካባቢው ሀገሮችን ጉብኝት በጀመሩበት ወቅት ነው።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬ ሪ (Kerry) ዛሬ ከቱኒዝያው አቻቸው ከጣይብ ባኮቸ (Taieb Baccouche) ጋር አንድ ላይ በታዩበት ወቅት፥ ዩናይትድ ስቴትስ እ አ አ በ 2011 ዓም ከ $700 ሚሊዮን ዶላር በላይ እርዳታ መስጠቷን አውስተው፥ አሁን ደግሞ ሌላ አዲስ የብድር ዋስትና ለመስጠት ማቀዷን አስታውቀዋል።

Baccouche በበኩላቸው፥ በጎረቤት ሊብያ ”አሸባሪነት ሥር እየያዘ መጥቷል” ብለው፥ በዚህም ምክንያት ለሃገራቸው የስጋት ምንጭ መሆኑን አስረድተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በድንበር ጥበቃው ጥረት ለማገዝ ቃል መግባቷን ቱኒዝያ በደስታ ትቀበላለች ሲሉም፥ የቱኒዝያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጣይብ ባኮቸ (Taieb Baccouche) አስረድተዋል።

VOA60 Africa- U.S. Secretary of State John Kerry visits Tunisia
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:00 0:00

XS
SM
MD
LG