በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያዋ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት

በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ጎንደርና ባህርዳር ግጭት መቀጠሉን ጠቅሶ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት /ስቴት ዲፓርትመንት/ የኅዳር 27ቱን ወደ ኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዛሬ አድሶ አውጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ በአማራ ክልል ጎንደርና ባህርዳር ግጭት መቀጠሉን ጠቅሶ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት /ስቴት ዲፓርትመንት/ የኅዳር 27ቱንወደ ኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ዛሬ አድሶ አውጥቷል፡፡

በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ጥቅምት 2006 ከታወጀ ወዲህ፤ ብጥብጥ ሊነሳና ካለሕጋዊ ትዕዛዝ መታሰር ሊከሰት ሰለሚችል የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ወደ ሀገሪቱ እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡

ዛሬ የወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ የኢትዮጵያ መንግሥት መጋቢት 6/2009 የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁን ማራዘሙን ጠቅሶ፣ በጎንደርና በባህርዳር አሁንም ግጭት መኖሩን ዘገባዎች ይጠቁማሉ ብሏል፡፡

ማስጠንቀቂያው የኢትዮጵያ መንግሥት በየጊዜው ኢንተርኔትና የእጅ ስልክ አገልግሎትን ሰለሚዘጋ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ውስጥ ላሉ የአሜሪካ ዜጎች ችግር ለመድረስና የምክር አገልግሎት መሰጠት ያዳግተዋል፤ ይላል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት የአሜሪካ ዜጎችን ቁጥጥር ሥር ሲያውል /ሲያሥር/ እንደሚጠብቀው ለኢምባሲው እንደማያሳውቅ ጠቅሷል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያው ዜጎቹ ከሕዝባዊ ተቃውሞ ወይም ስብስብ አንዲርቁ፣ ሁልጊዜም ያሉበትን አካባቢ ሠላም እንዲገመግሙና ለደኅንነታቸው እንዲጠነቀቁ አሳስቧል፡፡

የጉዞ ማስጠንቀቂያው ከአሁኑ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት ያወጣ ሰለሆነ ዝርዝሩን ከድረ ገፃችን ይመልከቱ፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ኢትዮጵያ የጉዞ ማስጠንቀቂያዋ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG