ዋሽንግተን ዲሲ —
በእንቦጭ አረም ምክኒያት የምጥፋት አደጋ ያንዣበበትን የጣና ሐይቅ ጉዳይ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ሆኗል። ሰሞኑን ደግሞ ከኦሮሚያ ክልል የተሰባሰቡ 200 ወጣቶች ወደ አማራ ክልል ተጉዘው "ታና ኬኛ" ወይም ጣና የኛ ነው በሚል በጋራ ሆነው አረሙን የማውጣት ሥራ ሠርተዋል።
ጽዮን ግርማ ይህ ሐሳብ እንዴት መጣ ስትል ከሁለቱ ክልልሎች ወጣቶችን አነጋግራለች።