በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የደቡብ ክልል ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አቤቱታ


የቀድሞው የደቡብ ክልል ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አቤቱታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:27 0:00

የቀድሞው የደቡብ ክልል ሠራተኞች የደመወዝ ክፍያ አቤቱታ

ከ700 በላይ የሚሆኑ የቀድሞው የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የውሃ ሥራዎች ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝ ለሁለት ወራት እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ።

ለከባድ ችግር መዳረጋቸውን ሠራተኞቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የውሃ ሥራዎች ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሐዲስ ዘካሪያስ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ድርጅቱ በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር ሲተዳደር እንደነበር አስታውሰው “የክልሉን መፍረስ ተከትሎ ድርጅቱ ችግር ላይ መውደቁን እና በተፈጠረው የገንዘብ እጥረት ምክንያት ለሠራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን” አብራርተዋል፡፡ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ሥራ ማቆሙንም ጠቁመዋል።

በክልሉ ስር የነበሩ ሌሎች ቢሮዎች፥ አቻ ድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች ከሠራተኞቻቸው ጋራ በአዳዲስ ክልሎች የተመደቡት ባለፈው ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ክልሎቹ እንደተመሰረቱ ቢሆንም የዚህ ድርጅት ዕጣ ምን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG