ከ700 በላይ የሚሆኑ የቀድሞው የደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የውሃ ሥራዎች ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝ ለሁለት ወራት እንዳልተከፈላቸው ተናገሩ።
ለከባድ ችግር መዳረጋቸውን ሠራተኞቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የውሃ ሥራዎች ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ ሐዲስ ዘካሪያስ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ድርጅቱ በቀድሞው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ስር ሲተዳደር እንደነበር አስታውሰው “የክልሉን መፍረስ ተከትሎ ድርጅቱ ችግር ላይ መውደቁን እና በተፈጠረው የገንዘብ እጥረት ምክንያት ለሠራተኞች ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን” አብራርተዋል፡፡ ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ስራ ማቆሙንም ጠቁመዋል።
በክልሉ ስር የነበሩ ሌሎች ቢሮዎች፥ አቻ ድርጅቶችና መስሪያ ቤቶች ከሠራተኞቻቸው ጋራ በአዳዲስ ክልሎች የተመደቡት ባለፈው ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ/ም ክልሎቹ እንደተመሰረቱ ቢሆንም የዚህ ድርጅት ዕጣ ምን እንደሚሆን እስካሁን አልታወቀም።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡