በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ መንግሥት በቅዳሜው ፍንዳታ ለተጎዱ ሰዎች 1 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ ቃል ገባ


በፍንዳታው በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት
በፍንዳታው በንብረት ላይ የደረሰው ጉዳት

የሶማሊያ መንግሥት ባላፈው ቅዳሜ በአገሪቱ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ቢያንስ 100 ሰዎችን በገደሉትና 300 የሚሆኑ ባቆሰሉት ሁለት የቦምብ ጥቃቶች ለተጎዱ ቤተሰቦች የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለመስጠት ቃል ገብቷል፡፡

በጥቃቶቹ ማግስት እሁድ በተካሄደ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ይህን ያስታወቁት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዛ ባሬ ናቸው፡፡

የገንዘብ ድጋፉ የተጎጂዎቹን ቤተሰቦችና የህክምና ወጭዎችን ለመሸፈን የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ቅዳሚ ስለደረሱት ስለሁለቱ የቦምቦ ፍንዳታዎች ዝርዝር መግለጫዎችን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በመጀመሪያው ፍንዳታ ኢላማ በተደረገው የትምህርት ሚኒስቴር ህንጻ ላይ አጥፍቶ ጠፊዎቹ በተሽከርካሪ ላይ የተጠመደ ቦምብ ሲያፈነዱ፡፡

ሁለተኛው ፍንዳታ ደግሞ የደረሰው በሞተር ቢስኪሌት በሚጎተት ተሳቢ ላይ በተጫኑ ቦምቦች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የቅዳሜው ጥቃት እአአ ጥቅምት 14/2017 በዚያው ስፍራ ከደረሰውና 1000 ሰዎች ከተገደሉበት እና ከቆሰሉበት ጥቃት ቀጥሎ በሞቱት ሰዎች ብዛት ሁለተኛው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

XS
SM
MD
LG