በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ውስጥ በቦንብ ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች እንደተገደሉ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አስታወቁ


ጥቃቱ እንቅስቃሴ ከሚበዛባቸው የከተማዋ ቀጠናዎች መካከል በአንዱ በሚገኘው የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ህንጻ ላይ ያነጣጠረ ነበር ።
ጥቃቱ እንቅስቃሴ ከሚበዛባቸው የከተማዋ ቀጠናዎች መካከል በአንዱ በሚገኘው የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ህንጻ ላይ ያነጣጠረ ነበር ።

በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሹ በሁለት መኪኖች ላይ በተጠመደ ቦንብ ጥቃት በትንሹ 100 ሰዎች እንደተገደሉ ፣ ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ለጉዳት መዳረጋቸውን የሶማሊያ ፕሬዚደንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ አስታወቁ ።

ጥቃቱ የደረሰበትን ስፍራ ዛሬ እሁድ ማለዳ የጎበኙት ፕሬዚደንት ሀሰን በጥቃቱ የቆሰሉትን የሚረዱ ሀኪሞች እና የህክምና ቁሳቁሶችን ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ እንዲልክ ተማዕነዋል ።የሀገሪቱ ህዝብ ወደ ሆስፒታሎች በመሄድ ደም እንዲለግስም ጠይቀዋል።በአሁኑ ጥቃት እና በሌሎች አልሸባብ በፈጸማቸው ጥቃቶች ምክንያት ብቻቸውን ለቀሩ ህጻናት ሀገራቸው ነጻ የትምህርት እንደምትሰጥም አክለዋል።

ጥቃቱ እንቅስቃሴ ከሚበዛባቸው የከተማዋ ቀጠናዎች መካከል በአንዱ በሚገኘው የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ህንጻ ላይ ያነጣጠረ ነበር ።ስፍራውን ከመጎብኘታቸው በፊት ፕሬዚደንት ሀሰን በቲዊተር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ጥቃቱን “የስነ-ምግባር ደሃ እና ወንጀለኛ በሆነው የአልሸባብ ቡድን ፣ በንጹሃን ላይ የተወሰደ ጨካኝ እና የወኔ ቢሶች የሽብር ጥቃት ነው “ ሲሉ አውግዘውታል ። የአሁኑ ጥቃት መንግስታቸው እና የሀገሪቱ ህዝብን ጥረቶች እንደማይቀለብስም አስታውቀዋል ።

በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ሞሃመድ ኢሴ ኮና የተባለ የሀገሪቱ ጋዜጠኛ ይገኝበታል። የቪኦኤው ሳማሊ ቋንቋ ዘጋቢ አብዱልቃድር ሞሃመድ አብዱል እና የሮይተርስ አውታር የፎቶ ጋዜጠኛ ፋይሰል ኦማር በጥቃቱ ጉዳት ደርሶባቸዋል ።

የአሜሪካ ድምጽ ከሰራተኞቹ መካከል አንዱ ለጉዳት መዳረጉ እንዳስደነገጠው ገልጾ ፣ ሁኔታውን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ እና ጋዜጠኛው ከጉዳቱ እስኪያገግም ድጋፉን እንደሚቸር አስታውቋል።

የሌሎች የዜና አውታር ባልደረቦችን ጨምሮ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ለሞት እና አካል ጉዳት ማደራጋቸውን እንደተገነዘበ ባወጣው መግለጫ ላይ የጠቀሰው ተቋሙ ፣ የጋዜጠኞቹ ጀብዱ እና አይበገሪነት፣ ዜና ወዳለበት ስፍራ ሁሉ የሚወስዳቸው ቁርጠኝነት ፣ ዘወትር ከአደጋ ጋር እንደሚያጋፍጣቸው አስታውሷል ። በመግለጫው በዘገባ ላይ ባሉ የቪኦኤ ጋዜጠኞች ላይ አደጋ የጣለውን የአሁኑን ጥቃት ጨምሮ ሁሉን አይነት ሞት እና ጉዳት የሚያስከትሉ የጭካኔ ድርጊቶችን እንደሚያወግዝ ተቋሙ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG