በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ ወደ ሃርጌሳ ሲያመራ የነበረን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አየር ክልሏ እንዳይገባ አገደች


የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ወደ ሶማሊላንድ መዲና ሃርጌሳ ሲያመራ የነበረን አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሶማሊያ ወደ አየር ክልሏ እንዳይገባ በመከልከሏ ለመመለስ መገደዱ ታውቋል።

የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው Dash 8-Q400 አውሮፕላን “አስፈላጊው ፈቃድ ስለሌለው ወደ ሶማሊያ የአየር ክልል እንዳይገባ ተከልክሏል” ሲል አስታውቋል።

“በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ሕግና በሶማሊያ ደንብ መሠረት በረርራዎች ከመነሳታቸው አስቀድመው ከመዳረሻ አገራት ፈቃድ ማግኘት አለባቸው” ብሏል ባለሥልጣኑ በመግለጫው።

የሶማሊያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ፈቃድ የሌላቸውን አውሮፕላኖች ወደ አገሪቱ የአየር ክልል እንዳይገቡ እንደሚከለክል መግለጫው በተጨማሪ አመልክቷል።

በሃርጌሳ አውሮፕላን ጣቢያ የሚገኙ ባለሥልጣናት በበኩላቸው፣ አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁትር 372-373 አውሮፕላን በሰላም ማረፉን በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች አስታውቀዋል። አውሮፕላኑ “መደበኛ መንገደኞችን” መያዙንና የተመለሰው አውሮፕላን ግን ሌላ የበረራ ቁጥር እንደነበረው አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተግባቦት ባለሙያ የሆኑት አቶ አሸናፊ ዘራይ፣ በቪኦኤ አማርኛ ክፍል ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ “ድርጅቱ ለተናጥል የሚዲያ ጥያቄዎች መልስ እንደማይሰጥ” እና “በቅርቡ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚጠራ” አስታውቀዋል።

የቪኦኤ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት በበኩሉ፣ በሶማሊያ እና በሶማሌላንድ የሚገኙ የአቪዬሽን ባለስልጣናትን ለማግኘት ሞክሮ እስከ አሁን እንዳልተሳካለት አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG