“የመገናኛ ብዙሐን ነፃነት እንደ ዘንድሮው ዓመት የከፋ ይዞታ ኖሮት አያውቅም” ይላል በፓሪስ መሰረቱን ያደረገው ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በዛሬው ዕለት ባወጣው ዓመታዊ ዓለም አቀፍ “የሚዲያ ነፃነት” መለኪያ የደረጃ ሰንጠረዥ።
“በአካል ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና እስራቶች የበረቱበት መንግሥታት የመናገር ነጻነትን የሸበቡበት ዓመት ነው ብሎታል” ሪፖርቱ።
“በተለይ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ በሚባሉ ሀገሮች የሚዲያ ነፃነት ያሽቆለቆለበት፣አፋኝ ሕጎች የወጡበት፣ በአካል ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችና እስራቶች የጨመሩበት ዓመት ነው። ዲሞክራስያዊ መንግሥታት በመርህ ደርጃ ተምሳሌት መሆን ሲገባቸው የሚዲያ ነፃነትን የሚፃረሩ ሆነዋል።” ብሏቸዋል የድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን በሪፖርቱ።
ኢትዮጵያ በዚህ በማያስመሰግነው ደርጃ ላይ ከመቶ 180 ሀገሮች 150 ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ቡድን ሲፒጄ በዚሕ ዓመት ሪፖርቱ ኢትዮጵያ 16 ጋዜጠኞችን በማሰርና የመናገር ነፃነት በማፈን ከአፍሪካ ሦስተኛ ሀገር ብሏታል።
በኢትዮጵያ የረጂም ጊዜ እስራት ከተበየነባቸው ጋዜጠኞች አንዱ ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ነው። እስክንድር ከትናንት በስቲያ መቀመጫውን ኦስትሪያ ቬና ካደረገው ዓለም አቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት “የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” የሚል ስያሜ አግኝቷል ባለቤቱን ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲልን አነጋግረናታል።
በዚህ ሰንጠረዥ ሰሜን ኮሪያ የመጨረሻውን ደረጃ ስትይዝ ኤርትራ በአንድ ደረጃ ከፍ ብላ ትከተላለች። ኖርዌይ ስዊድን ፊንላንድ ዴንማርክና ኔዘርላንድስ በዓለማችን ጋዜጠኞች በነጻነት ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑባቸው ሀገሮች ሆነዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ