ዋሽንግተን ዲሲ —
በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ መቀመጫውን ኦስትሪያ ቬና ባደረገው በዓለም አቀፉ ፕሬስ ኢንስቲትዩት የዚህ ዓመት “የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” ተባለ።
ተቋሙ ይህን ሽልማት ህይወታቸውን መስዋት አድርገው በንግግር ነፃነት የጎላ አስተዋጾ ያበረከቱ ጋዜጠኞችን መርጦ እንደሚሸልም አስታውቋል።
“የአፍጋኒስታን ጋዜጠኞች ደህንነት ኮሚቴም” ሁለተኛው “የዓለም የፕሬስ ነፃነት ጀግና” ተብሏል።
ጽዮን ግርማ የተቋሙን የአድቮኬሲና የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ስቲቨን ኤሊስን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባለች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ