በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የከለላ ጠያቂዎች ምዝገባ መቋረጥ አሳስቦኛል” ዩኤንኤችሲአር


“የከለላ ጠያቂዎች ምዝገባ መቋረጥ አሳስቦኛል” ዩኤንኤችሲአር
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:47 0:00

“የከለላ ጠያቂዎች ምዝገባ መቋረጥ አሳስቦኛል” ዩኤንኤችሲአር

በኢትዮጵያ ከሦስት ዓመታት በላይ ለሆነ ጊዜ የተቋረጠው የከለላ ጠያቂዎች ምዝገባና ሰነድ የማግኘት ችግር እንዳሳሰበው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር /UNHCR/ አስታወቀ፡፡ ተቋሙ፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት፣ የተቋረጠውን ምዝገባ እንዲያስጀምሩ ጠይቋል፡፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በሀገሪቱ የስደተኞችና ከለላ ጠያቂዎች ምዝገባ መቋረጥ፣ በነፃነት የመንቀሳቀስ መብታቸውን እንደገደበ እና ሌሎችም ችግሮችን እያሰከተለ እንደሆነ፣ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡

ኮሚሽኑ፣ ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ከ950 ሺህ በላይ ስደተኞች ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣቸውን ያመለክታል፡፡ በኮሚሽኑ፣ የስደተኞች፣ የፍልሰተኞች እና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መብቶች ክፍል ዳይሬክተር እንጉዳይ መስቀሌ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሪፖርቱ ከምዝገባ እና ሰነድ ከማግኘት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ችግር፣ ትልቅ ትኩረት የሚሻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የዚህ አገልግሎት ከሦስት ዓመታት በላይ መቋረጥ፣ ስደተኞችን እና ከለላ ጠያቂዎችን ለችግር እንደዳረጋቸውም አመልክተዋል፡፡

ስለጉዳዩ በአሜሪካ ድምፅ የተጠየቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር /UNHCR/ በበኩሉ በኢሜይል በሰጠው ምላሽ፣ “ስደተኞች እና ከለላ ጠያቂዎች የሚመዘገቡበትና አስፈላጊውን ሰነድ የሚያገኙበት ሒደት አለመጀመሩ አሳስቦኛል” ብሏል፡፡ በስደተኝነት አለመመዝገብና ህጋዊ ሰነድ አለመያዝ፣ የስደተኞችን እና ከለላ ጠያቂዎችን በነፃነት የመንቀሳቀስ መብት ከመገደቡም ባሻገር፣ ለእስርና በግድ ወደ ሀገራቸው ለመባረር እየዳረጋቸው እንደሆነ ገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት፣ ምዝገባውን እንዲያስጀምሩ እየወተወትን ነን” ሲልም አስታውቋል፡፡

ስደተኞቹና ከለላ ጠያቂዎቹ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ዕጥረት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሪፖርቱ ያመለከተ ሲሆን “ችግሩ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካው ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት እርዳታ ባቋረጡበት ወቅት ተባብሶ የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም የድጋፍ አጥረቱ እየታየ” መሆኑን እንጉዳይ መስቀሌ አመልክተዋል፡፡

የመጀመሪያው ከተቀባይ ማሕበረሰቦች ጋር በሚከሰቱ ግጭቶች የሚደርስባቸው ጉዳት ነው፡፡ ሌላው በሀገራችን የተከሰተውን ግጭት ወይም ጦርነት ጨምሮ ስደተኞች በሚኖሩባቸው አንዳንድ ክልሎች በሚከሰቱ ግጭቶች በታጣቂ ኅይሎች የሚፈጸሙባቸው ጥቃቶች ለከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንዲሁም ጉዳቶች እንደዳረጋቸው ባከናወንናቸው ምርመራዎች አእረጋግጠናል”

የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር/UNHCR/ በበኩሉ ፣ በስደተኞች ዘንድ የሚታየው የሰብዓዊ ድጋፍ እና የማህበራዊ አገልግሎት ችግር፣ በገንዘብ እጥረት ምክንያት መፈጠሩን አመልክቷል፡፡ ከዓለም አቀፍ ለጋሾች የሚገኘው ገንዘብ፣ ችግር ላይ ያሉት ከሚያስፈልጋቸው ግማሽ ያህሉን እንኳ እንደማይሸፍን የገለፀው ተቋሙ፣ በኢትዮጵያ ላሉት ስደተኞች መርጃ ከጠየቀው የ431.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ውስጥ፣ ማግኘት የቻለው 36 ከመቶ ብቻ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ለጋሾች አሁንም፣ የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉም ተማፅኗል፡፡ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽኑ ሪፖርት፣ በስደተኞች ዘንድ የአደጋ ስጋት ፈጥሯል ያለው ሌላው ችግር፣ ከፀጥታ ጋር የተያያዘ መሆኑን እንጉዳይ መስቀሌ አስረድተዋል፡፡

“የመጀመሪያው ከተቀባይ ማሕበረሰቦች ጋር በሚከሰቱ ግጭቶች የሚደርስባቸው ጉዳት ነው፡፡ ሌላው በሀገራችን የተከሰተውን ግጭት ወይም ጦርነት ጨምሮ ስደተኞች በሚኖሩባቸው አንዳንድ ክልሎች በሚከሰቱ ግጭቶች በታጣቂ ኅይሎች የሚፈጸሙባቸው ጥቃቶች ለከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች አንዲሁም ጉዳቶች እንደዳረጋቸው ባከናወንናቸው ምርመራዎች አእረጋግጠናል” ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የመንግሥታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፣ “በተለይም በአማራ ክልል ያለው ግጭት፣ የስደተኞችን የመንቀሳቀስ ነፃነት በመገደቡ፣ ለጥቃት በማጋለጡ እና የእርዳታ አቅርቦትንና ማህበራዊ አገልግሎትን በማስተጓጎሉ፣ አሳሳቦኛል” ብሏል፡፡ የሚመለከታቸው አካላትም፣ የስደተኞችን ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ሐላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲል ጠይቋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት የኮሚዩኒኬሽንና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ በአካል ንጉሤ፣ በሰብአዊ መብቶች ኮሚሽኑ ሪፖርት የተነሱ ጉዳዮችን በሚመለከት ፣ “በቅርቡ ምላሽ እንሰጣለን” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG