በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ኦባማ ትላንት ወደ አርጀንቲና ከማምራታቸው በፊት ለኩባ ህዝብ ያደረጉት ጥሪ


ፕረዚዳንት ኦባማ ትላንት ወደ አርጀንቲና ከማምራታቸው በፊት ለኩባ ህዝብ ባደረጉት በብሄራዊ ቴሌቪዥን በታየ ንግግር ኩባ ውስጥ ዲሞክራስያዊ ለውጥ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። በሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ላይም ትኩረት ሰጥተዋል።

ከአስራ አምስት ወራት በፊት አንድ አሜሪካዊ ፕረዚዳንት በቀጥታ ለኩባ ህዝብ ንግግር ሊያደርግ የሚችልበት ዲፕሎማስያዊ ሁኔታ አልነበረም።

“እዚህ የመጣሁት በአሜሪካ ሃገሮች የመጫራሻውን የቀዝቃዛ ጦርነት ርዝራዥን ለመቅበር ነው።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ በሀቫና ግራንድ ማለት ታላቅ ትያትር ቤት ሆነው ባደረጉት ንግግር ዩናይትድ ስቴትስንና ኩባን “ለብዙ አመታት ተራርቀው የቆዩ ወንድማማቾች” ብለዋቸዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ የኩባው ፕረዚዳንት ራኡል ካስትሮና ሌሎች የሀገሪቱ ባለስልጣኖች በአደራሹ ተቀምጣው ያዳምጡ በነበረው ንግግራቸው ስለ-ሰብአዊ መብት ወሳኝነት አስገንዝበዋል።

“ዜጎች ካለ ምንም ፍርሀት የመሰላቸውን የመናገር ነጻነት ሊኖራቸው ይገባል። የመደራጀት፣ መንግስታቸውን የመንቀፍና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ የማካሄድ ነጻነት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። በህግ የመገዛት ጉዳይ እነዚህ መብቶችን የተጠቀሙ ሰዎችን በዘፈቀ ማሰርን nማቀፍ የለበትም። ሰዎች መንግስታቸውን ነጻና ዲሞክራስያዊ በሆነ የምርጫ ሂደት ለመምረጥ መቻል አለባቸው ብየ አምናለሁ።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ አያይዘውም ዩናይትድ ስቴትስ በኩባ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እንዲነሳ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።

“በዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንትንቴ በኩባ ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ ለሀገሪቱ ምክር ቤት ጥሪ አቅርቤያለሁ። ማዕቀቡ በኩባ ህዝብ ላይ የተጫነ ጊዜ ያለፈበት ሽክም ነው። በኩባ መስራት፣ ከኩባ ጋር የንግድ ስራ ማካሄድ ወይም በኩባ መዋዕለ-ነዋይ ለማፍሰስ በሚፈልጉ አሜሪካውያን ላይ የተጫነ ሸክምም ነው። ማዕቀቡ መነሳት ያለበት ጊዜ ደርሷል።” በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ባለፈው እሁድ ኩባ እንደገቡ የኩባ ባለስልጣኖች ዲሞክራሲን በመደገፍ የተካሄደ ተቃውሞን በትነዋል። አስረዋልም።

ፕረዚዳንት ኦባማ ትላንት ማክሰኞ ንግግር ካደረጉ በኋላ በሀገሪቱ ካሉት ተቃውሚዎች ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል። ባለፈው እሁድ ተይዘው የነበሩ ተቃዋሚዎችም ይገኙባቸዋል።

“ተይዘው የነበሩ ሰዎችም እዚህ አሉ። አንዳንዶቹ በፊት ሌሎቹ ደግሞ በቅርቡ ተይዘው የነበሩ። ከዚህ ቀደምም ደጋግሜ እንደተናገርኩት ሁሉ ከኩባ ጋር በሚኖረን የግንኙነት ፖሊሲ መሰረት ከፕረዚዳንት ካስትሮና ሌሎች ባለስልታኖች ጋር ተገናኝቶ መነጋገር ብቻ ሳይሆን የኩባ ህዝብ የሚለውን በቀጥታ ከራሱ ለመስማት መቻልም ጭምር ነው።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ የኩባ ጉብኝታቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት በታምፓ በይ ሬይስና በኩባ ብሄራዊ ቡድን መካከል በቤዝባል ስታድዮም የተደረገ የቤዝ ቦል ጨዋታ ውድድር አውደ-ትርኢት ተመልክተዋል። ከኩባ መሪዎች ጋር አብረው የጨዋታ ውድድር ለማየት የቻሉበትን ጊዜ “በጋራ ያሳለፍነው ብሄራዊ የመዝናኝ ጊዜ” ብለዋታል። ሁለቱ ሀገሮች የአንድነት ስሜት ያንጸባረቁበት ጊዜ ሆኗል።

ዘጋብያችን አልበርቶ ፒሚየንታ (Alberto Pimienta) ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ፕረዚዳንት ኦባማ ትላንት ወደ አርጀንቲና ከማምራታቸው በፊት ለኩባ ህዝብ ያደረጉት ጥሪ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:37 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG