በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጎርፍ በተጥለቀለቀው ምሥራቅ ኮንጎ ከ5ሺሕ500 በላይ ነዋሪዎች ፍለጋ ቀጥሏል


በጎርፍ በተጥለቀለቀው ምሥራቅ ኮንጎ ከ5ሺሕ500 በላይ ነዋሪዎች ፍለጋ ቀጥሏል
በጎርፍ በተጥለቀለቀው ምሥራቅ ኮንጎ ከ5ሺሕ500 በላይ ነዋሪዎች ፍለጋ ቀጥሏል

ባለፈው ሳምንት፣ ከ400 የሚበልጡ ሰዎች በጎርፍ በተወሰዱበት የምሥራቅ ኮንጎ አካባቢ፣ እስከ አሁን የደረሱበት ያልታወቀ፣ ከ5ሺሕ500 በላይ ሰዎች መኖራቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ።

በጎርፍ አደጋው በከባድ ድንጋጤ የተዋጡ ነዋሪዎች፣ ዛሬ የምግብ ርዳታ ለመቀበል ተኮልኩለው ሲጠባበቁ ታይተዋል፡፡ በሁለት የደቡብ ኪቩ ክፍለ ግዛት መንደሮች፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ በደረሰው የመሬት መንሸራተት እና ደራሽ ጎርፍ ሳቢያ የሞቱ በርካታ ሰዎች አስከሬኖች ሲገኙ፣ በአደጋው ሕንፃዎች ፈራርሰዋል። ጎርፉ፥ የአካባቢውን ሰብል ጠራርጎ ወስዷል።

ከአደጋው ሰለባዎች የሚበዙት ሴቶች እና ሕፃናት፣ በሳምንቱ መጨረሻ በአንድ ላይ ሲቀበሩ፣ “ግብአተ መሬታቸው የተፈጸመው ክብር በጎደለው መንገድ ነው፤” በሚል፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ቅሬታ አሰምተዋል።

የቀይ መስቀል ሠራተኞች በበኩላቸው፣ በአደጋው የተጎዱትን ነዋሪዎች ለመርዳት የሚያስፈልገው አቅርቦትና የመሣሪያ እጥረት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

በኮንጎ ታሪክ ከደረሱት ከባድ የተፈጥሮ አደጋዎች አንዱ በኾነው በዚኽ የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በርካታ ሰዎች ያለመጠጊያ ቀርተዋል። እስከ አሁን፣ የ411 ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲኾን፣ 5ሺሕ525 ሰዎች መዳረሻ ገና አለመታወቁን ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG