በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 170 ሰዎች ሞቱ


ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 3፣ 2023
ፎቶ ኤፒ ሚያዚያ 3፣ 2023

በኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በደረሰ የጎርፍ አደጋ 170 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲሉ ባለሥልጣናት ትናንት አስታውቀዋል።

በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ የደረሱበት አልታወቀም ተብሏል። በመቶ የሚቆጠሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል። የሟቾች ቁጥርም ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን ይቻላል ተብሏል።

በአደጋው የሞቱትን ለማሰብ ሰኞ ብሔራዊ የሀዘን ቀን እንደሚሆን የኤኤፍ ፒ ዘገባ አመልክቷል።

በሌላ በኩል ሰሞኑን በሩዋንዳ የጣለው ዝናብ ያስከተለው ጎርፍና የመሬት መንሸራተት የ131 ሰዎችን ሕይወት ከቀጠፈ በኋላ፣ ለወደሙ መሠረተ ልማቶች መጠገኛ 100 ሚሊዩን ዶላር አገሪቱ መድባለች.።

9 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎችን ካለመጠለያ ባስቀረው አደጋ፣ የት እነደደረሱ እስከአሁን ያልታወቁ በርካታ ሰዎችም አሉ ተብሏል። 50 የሚሆኑ ት/ ቤቶችም ወድመዋል።

XS
SM
MD
LG