በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኮንጎ የጎርፍ መጥለቅለቅ የሟቾች ቁጥር ወደ 400 አሻቅቧል

ባለፈው ሳምንት፣ ዴሞክራሲያዊት ኮንጎ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ክፍለ ግዛት ውስጥ በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 400 እየተቃረበ መኾኑ ተገልጿል፡፡

በጎርፉ የተወሰዱና እስከ አሁን ዳናቸው ያልተገኘ በርካታ ሰዎች መኖራቸውን፣ ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋል፡፡

በተለይ፣ ኢኒያሙኩቢ እና ቡሹሹ በተባሉት መንደሮች የጣለው ዝናም፣ እጅግ ከባድ እንደነበር ታውቋል፡፡

የሞቱት ሰዎች በጣም ከመብዛታቸው የተነሣ፣ የመንደሩ ነዋሪዎች፣ አስከሬኖቹን በጅምላ ለመቅበር መገደዳቸው ተመልክቷል፡፡ የኮንጎ መንግሥት በዐወጀው መሠረት፣ ዛሬ ሰኞ፣ የጎርፍ ሰለባዎቹ የሚታሰቡበት ብሔራዊ የኀዘን ቀን ኾኖ ውሏል፡፡

ባለፉት ቅርብ ቀናት፣ በኬኒያ እና በዩጋንዳ ውስጥም፣ ከባድ ዝናም መጣሉ ታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG