በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማላዊያን ያልሆኑ በደዳብ የተጠለሉ ስደተኞች የካምፑ መዘጋት ያሳስበናል አሉ


ደዳብ የስደተኞች ካምፕ
ደዳብ የስደተኞች ካምፕ

የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ መዘጋት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ እንደሚጥለው ቁጥራቸዉ አነስተኛ የሆነ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የኤርትራ፣ የቡሩንዲ እንዲሁም የሌሎች ሃገሮች ስደተኞች ገለጹ።

አንዲት ለ7 ዓመት በዳዳብ የኖረች ኢትዮጵያዊት ወጣት፣ “ለሶማሊያ ስደተኞች ወደ ትዉልድ አገራቸዉ የሚመለሱበት መንገድ ሲመቻች ወደ አገሮቻችን ተመልሰን መኖር ለማንችል ሌሎች አገሮች ስደተኞች ምንም መፍትሄ እየተፈለገልን አይደለም” ትላለች።

ኬንያ የሚገኘዉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ቅርንጫፍ ቃልአቀባይ ዱክ ምዋንቻ ስለጉዳዩ ተጠይቀዉ ድርጅታቸዉ ለጉዳዩ መፍትሄ ለመስጠት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመስራት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ዳዳብ የስደተኞች ካምፕ
ዳዳብ የስደተኞች ካምፕ

በሌላ በኩል የኬንያ መንግስት የስደተኞችን ጉዳይ የሚከታተል አዲስ መዋቅር እንዳደራጀም እየተነገረ ነዉ።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ሶማላዊያን ያልሆኑ በደዳብ የተጠለሉ ስደተኞች የካምፑ መዘጋት ያሳስበናል አሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG