ዋሽንግተን ዲሲ —
ዛሬ ጥምቀት ነው። ለተከበራችሁ የእምነቱ ተከታዮችና ለአድማጮቻችንም፣ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ በማለት ከአሜሪካ ድምፅ ራድዮ አፍሪቃ ቀንድ አገልግሎት መልካም ምኞታችንን እንገልጻለን።
አለው አለው ሳቢሳ፣ አለው ሳቢሳ
ቅዱስ ጊዮርጊስ (ቅዱስ ገብሬል - -) ሲነሳ
አለው አለው ብር ዋንጫ፣ አለው ብር ዋንጫ
የስላሴ መጠጫ -- እያሉ፣ ምእመናን፣ ሴቶች በእልልታ፣ ወንዱ ደግሞ በሆታ ታቦታቱን አጅበው ይጓዛሉ። ይህ፣ ከኢትዮጵያ የጥምቀት አከባበር አንዱና የተለመደው ክፍል ነው።
ለመሆኑ ጥምቀት ለአማንያኑ ምን ትርጉም አለው? አዲሱ አበበ ለተለያዩ የእምነቱ ተከታዮች ያቀረበው ጥያቄ ነው። ከዚሁ ጋር፣ "ምን ዓይነት የጥምቀት ትዝታ አለዎ?" በማለትም የሃይማኖቱን ተከታዮች ምእመናን ጠይቋል።
የአንድ ሁለቱ አስተያየት በቀጣዩ ቅንብር ውስጥ ተካቷልና ሙሉውን ዝግጅት በድምጽ ፋይሉ ያገኙታል፣ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።