በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዳማ ዩኒቬርሲቲና በምስራቅ ሃረርጌ የተቃዉሞ ሰልፎች መካሄዳቸዉ ታዉቋል


በአዲስ አሰባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልማት ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን እቅድ የተባለዉን በመቃወም ዛሬም በኦሮሚያ ልዩ ልዩ አካባቢዎት የተቃዉሞ ሰልፎች ተካሄዷል። በዛሬዉ እለት በአዳማ ዩኒቬርሲቲና በምስራቅ ሃረርጌ የተቃዉሞ ሰልፎች መካሄዳቸዉ ታዉቋል።

እንደሰሞኑ ሁሉ የአድማ በታኝን የመከላከያ ሃይሎች ሰልፈኞች ላይ ጥቃት አድርሰዋል። በሌላ በኩል ባለፈዉ ሳምንት በዲላ ዩኒቬርሲቲ ከደረሰዉ የቦምብ ፍንዳታና ግድያ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ግቢዉን ለቀዉ እንዲወጡ መደረጋቸዉ ተገልጿል።

ዛሬ ማለዳ በአዳማ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች የፊኒንፌኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልማት ዞን የተቀናጄ ማስትር ፕላን የተባለዉን መቃወማቸዉን ከስፍራዉ ያነጋገርነዉ ተማሪ ገልጾልናል። “በአሁኑ ሰዓት በዩኒቬርሲቲዉ የሚገኙ የጸጥታ ሃሎች የኦሮሞ ተማሪዎችን ከሌሎች ተማሪዎች እየለዩ ወደ ቅጥር ጊቢዉ እንደሚመልሱ የገጸልን ስማ እንዳይገለጽ የጠየቀ ተማሪ ጥቃት እንዳይደርስብን ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ነን ብሎል። ዩኒቬርሲቱዉ የጦር ሰፈር እንጂ የትምህት ተቋም እንደማይመስል ጠቅሶ ቁጥጥር ስር ስለዋሉ ተማሪዎችም ገሏል” ብለዋል።

ይህ በእንዲ እንዳለ በምስራቅ ሃረርጌ የቆቦ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ከጥዋቱ አንስ ሰዓት ጀምሮ እስከ አስራ አምስት ሰዐት ተኩል ድረስ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸዉ ተገልጾል። ሰልፈኞቹ ከአካባቢዉ ገጠሮች በሶስት አቀእጣጫዎች ወደ ከተማዋ እንደገቡ ስማቸዉ እንዳይገለጠ የጠየዉ የሰልፉ ተካፋዮች ገልጸዉልናል። የኦሮሚያ ፓሊስ ሰልፉን እንዲቆሙ ቢያዝም ሕዝቡ ባላማቆሙ ሌላ ተጨማሪ ሃይል ወደ ወደ ከተማዋ መግባቱን ስማቸዉ እንዳይገልጥ የጠይቁ የአይን እማኝ ገልጸዋል።

“ሰልፉ ትንሽ እንደቆየ አጋአዚ የሚባለዉን ሃይል ጨምረዉ በማምጣት ተኩስ ከፈቱ። ሰልፉም ተበተነ። ነጋዴዎችና ሌላዉ ነዋሪዎች ህዝብ ከሶስት እቅጣጫ ወጥቶ ስለነበር ብዙ ነበር ሕዝቡ። ሕዝቡ በሩን ዝግቶ ነዉ የወጣዉ” ብለዋል።

አቶ አህመድ ሙሚ የተባሉ የቆቦ ከተማ ነዋሪ በሰልፉ ላይ አናታቸዉን በዱላ ተመተዉ መቁሰላቸዉ ተገልጾል። የመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ወደ ሰማይ እየተኮሱ ሰልፈኛዉን እንደበተኑ ሰልፈኞች ይናገራሉ። ተጨማሪ የፌደራል ሃይል ወደ ከተማዋ እየገባና የከተማዋ ፖሊሶች ደግሞ ከቤት እቤት በመዘዋወር የሰልፉን ተካፋዮች እያደኑ መሆኑ በነዋሪዎቹ ተገልጿል። የቆቦ ከተማ ሱቆችና ምግብ ቤቶች ዝግ ናቸዉ ከተማዋም ከሚዘዋዋሩባት የጸጥታ ሃይሎቹ በስተቀር ጭር ብላለች ተብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ የዲላ ዩኒቬርሲቲ ተማሪዎች በብዛት የትምህት ቤት ቅጥር ጊቢዉን ለቀዉ እየወጡ መሆናቸዉ ታዉቋል። የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ባልደረባችን ስልክ ያነጋገረማሪ ዩኒቬሪሲቲዉ ተማሪ ባለፈዉ ሳምንት በቦምብ ፍንዳታ የሁለት ተማሪዎች ሕይወት ካለፈ ወዲህ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች ተቃጥለዋል ብሎአል።

ሌሎች ሁለት ተማሪዎች ደግሞ ተገድለዉ አስከሬናቸዉ መታጠቢያ ቤት ዉስጥ እንደተገኘና ሌላ አንድ ተማሪ መሰከሬን ደግሞ በዩኒቨርሲቲዉ አቅራቢያ በሚገኝ ደን ዉስጥ እንደተገኘ ተነግሯል።

የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ክፍል ባለደረባችን ነሞ ዳንዲ ያጠናቀረዉን ትዝታ በላቸዉ አቅርባዋለች። ዘገባውን ከተያያዘው የምድጽ ፋይል ያዳምጡ።

በአዳማ ዩኒቬርሲቲና በምስራቅ ሃረርጌ የተቃዉሞ ሰልፎች መካሄዳቸዉ ታዉቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00

XS
SM
MD
LG