በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል


በጅማ ከተማ ማንነታቸው ባለታወቁ ወገኖች፣ የተወረወረ ቦምብ ጉዳት አደረሰ፡፡

በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል - ከትላንቱ በባሰ ተጠናክሯል ይላሉ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች።

በሌላ በኩል ነጋዴዎች የዘጓቸውን መደብሮች እንዲከፍቱ፣ የመንግሥት ኃይሎች እያስገደዱ መሆናቸውና ያልከፈቱትን እያሸጉ እንደሚሄዱ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪነት የተሠማሩና በአድማው የሚሳተፉ መኪኖችን፣ ሰሌዳዎች እየፈቱ እንደሚወስዱ እማኞች ያስረዳሉ።

በአንዳንድ ከተሞች፣ ወታደሮች በኃይል አስገድደው ያስከፈቷቸውን መደብሮችና ምግብ ቤቶች፣ ወታደሮቹ ዞር ሲሉ ነጋዴዎች መልሰው እየዘጉ “ያይጥና ድመት” ዓይነት ጨዋታ በመካሄድ ላይ ነውም ተብሏል።

ዛሬ በጅማ ከተማ እንዲያውም ሁኔታዎች ክፍተው፣ ማንነታቸው ባልታወቀ ወገኖች የተወረወረ ቦምብ በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተዘግቧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በኦሮሚያ ክልል የሥራ ማቆም አድማ ቀጥሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:27 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG