በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

61 ሰዎች ሞተዋል፣ 806 ቤቶች ተቃጥለዋል ፣ 14 ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል


በመቱ ከተማ በዛሬው ዕለት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ
በመቱ ከተማ በዛሬው ዕለት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና የአካባቢው ማኅበረሰብ አባላት ያካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍ

በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ውስጥ በሁለት ወረዳዎች በሁለት ቀን ብቻ 32 የሶማሌ ብሔረሰብ አባላትና 29 የኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ሕይወት ማለፉን የክልል ባለሥልጣናት እየተናገሩ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ የተፈፀመ ግድያ ነው ያሉብት ጋዱሉ ውስጥ ፖሊስ ጣቢያ እንደሌለ የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ገለፁ።

በኦሮሚያ ክልል ግድያና የተቃውሞ ሰልፍ በየቀኑ እየተሰማ ነው። በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በሐዊ ጉዲና ዳሮ ለቡ ወረዳዎች ውስጥ በሁለት ቀናት እስካሁን የ61 ሰው ሕይወት ጠፍቷል። ከ800 በላይ ቤቶች ተቃጥለዋል ከ14 ሺሕ በላይ ሰዎች ከቀያቸው መሰደዳቸውን የዞኑ ባለስልጣናት እየገለጹ ነው።

የኦሮሚያ ክልል ግጭቱ የተፈጠረው የሶማሌ ልዩ ኃይል ፖሊስ ድንበሩን አልፎ በጀመረው ጦርነት መክኒያት የተፈጠረ ነው ሲል የሶማሌ ክልል ደግሞ ጅምላ ጭፍጨፋ ነው ብሎታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝም በጅምላ የተፈፀመ ግድያ ነው ብለውታል።

የኦፌኮው አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው ሁሉም ነገር የተፈፀመው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመሩት ሀገር ውስጥ ነው ለዚህ ኃላፊነቱን መውሰድ ያለበት እርሳቸው የሚመሩት መንግስት ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል በቄለም ወለጋ ዞን በደንቢ ዶሎ ከተማ፣ በኢሊባቦር ዞን በመቱ ከተማ ግድያ ይቁም የሚሉና በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሚቃወሙ ተቃውሞዎች እየተካሄዱ መሆኑን ነዋሪዎችና የዞን ባልሥልጣናት ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

61 ሰዎች ሞተዋል፣ 806 ቤቶች ተቃጥለዋል ፣ 14 ሺሕ ሰዎች ተፈናቅለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:54 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG