በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ውይይት ከኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር


አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በሰጡት ቃለ-ምልልስ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል።

ሰሞኑን ኢትዮጵያ ውስጥ ለተቀሰቀሰው ሁከት ምክንያቱ በ 2006 ዓ.ም. ተዘጋጅቶ የቀረበው የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን መሆኑ ይነገራል። ማስተር ፕላኑ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና በአዲስ አበባ አስተዳደር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቶች መጽደቅ ይኖርበታል ተብሏል።

ምክር ቤቶቹ ሕዝብ እንዲገነዘበውና እንዲያምንበት ለማድረግ እንዲወያይበት ለማድረግም ወስነው ሳለ ሕዝቡ እስካሁን ማለትም ላለፉት አንድ ዓመት ተኩል በላይ በሰነዶቹ ላይ አልተወያየም። ለምን ለዚህን ያህል ጊዜ ዘገየ?

በዚህ እና በጎንደር በተከሰተው ግጭት እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮች ላይ ማብራርያ ሰጥተዋል። ሙሉ ዘገባውን ከሰሎሞን ክፍሌ ጋር ካደረጉት ቃለ-ምልልስ ያድምጡ።

ከኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ውይይት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:38 0:00

XS
SM
MD
LG