ዋሽንግተን ዲሲ —
በሪፖርቱ በአባባሽነትና በ”ዐመፅ” ጠሪነት ከተጠቀሱት የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ አንዱ ሲሆን ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ሙላቱ ገመቹ " ራሱ መስካሪና ራሱ ፈራጅ ነው። ቀጪውም፣ መርማሪውም ሁሉንም ያደረገው እርሱ ነው። ይሄ ትክክለኛ ሪፖርት ነው ብለን አንቀበለውም" ብለዋል።
የሰማያዊው ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሸዋስ አሰፋ፤ "ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም የገለልተኝነት ጥያቄ የቀረበበት ነው። ለአንድ አካል ያደላ እና ለፓርቲ የቀረበ አቋም ያለው ነው" ካሉ በኋላ በእንዲህ ያለ አካል የቀረበ ሪፖርት ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም ብለዋል።
የኦሮሞሚያ ሚዲያ ኔትወርክ እና የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴቭዥን ኃላፊዎችም ምላሽ ሰጥተዋል።
ያነጋገረቻቸው ጽዮን ግርማ ናት በተከታዩ ሪፖርት ይዛዋለች።
ዝርዝሩን ለማግኘት የድምፅ መጫወቻ ፋይሉን ይጫኑ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ