በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዶ/ር መረራ በማዕከላዊ ለመቆየት ጠየቁ


ዶ/ር መረራ ጉዲና
ዶ/ር መረራ ጉዲና

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው አመለከቱ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ተከሣሽ ባቀረቡት የዋስ ጥያቄ ላይ አስተያየቱን በፁሑፍ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

ዶ/ር መረራ ጉዲና በዋስ እንዲፈቱና ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ ጠበቆቻቸው አመለከቱ፡፡ ዓቃቤ ሕግ ተከሣሽ ባቀረቡት የዋስ ጥያቄ ላይ አስተያየቱን በፁሑፍ እንዲሰጥ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡ ከዶ/ር መረራ ጋር ተከሰው ያልቀረቡ ተከሳሾች፣ በጋዜጣ እንዲጠሩ ታዝዟል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ዶ/ር መረራ ጉዲና እንደቀረቡ ችሎቱን በመሰየሙ ሂደት ላይ፣ የሌሎች ተከሳሽ ስም ማለትም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ ጃዋር መሃመድ፣ ኢሳት ወይንም የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፣ ኦሮሞ ሚዲያ ኔት ወርክ ተጠርተው በስፍራው አለመኖቸው ተረጋግጧል፡፡ በመቀጠልም ዓቃቤ ሕግ ካቀረበው የክስ ማመልከቻ ላይ ዶ/ር መረራ ጉዲናን የሚመለክተውን ክፍል ፍ/ቤቱ ለተከሳሽ አንብቧል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

ዶ/ር መረራ በማዕከላዊ ለመቆየት ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:51 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG