በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፋኖ ታጣቂዎች በመንዲዳ ከተማ ስምንት ገበያተኞችን እንዳገቱ ተገለጸ


የፋኖ ታጣቂዎች በመንዲዳ ከተማ ስምንት ገበያተኞችን እንዳገቱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:48 0:00

የፋኖ ታጣቂዎች በመንዲዳ ከተማ ስምንት ገበያተኞችን እንዳገቱ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አቢቹ እና ኘዓ ወረዳ የመንዲዳ ነዋሪዎች የኾኑ ስምንት ሰዎች፣ በፋኖ ታጣቂዎች እንደታገቱ፣ ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ፡፡

ታጋቾቹ፣ ትላንት ገበያ ውለው እየተመለሱ የነበሩ ሰላማዊ ሰዎች እንደሆኑ፣ አስተያየት ሰጪዎቹ ገልጸዋል። የወረዳው ኮምዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ አብደታ ኃይልዬ፣ “ሁኔታው አሳሳቢ ነው፤” ብለዋል፡፡በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ታጣቂዎች በበኩላቸው፣ ስምንቱን ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር እንዳዋሏቸው ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገረው፣ አንድ የፋኖ ታጣቂ አባል እንደኾነ የገለጸ አስተያየት ሰጪ፣ “ግለሰቦቹ የተያዙት፣ የስለላ ሥራ በመሥራት ላይ እያሉ ነው፤” ብሏል፡፡ ኾኖም፣ “ማጣራት የምንፈልገውን ጉዳይ ስላጠናቀቅን፣ መንገድ ከተከፈተ ያለቅድመ ሁኔታ እንለቃቸዋለን፤” ሲል አክሏል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG