በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብተው ፈጽመዋል የተባለውን ጥቃት አስተባበሉ


የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብተው ፈጽመዋል የተባለውን ጥቃት አስተባበሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:07 0:00

የፋኖ ታጣቂዎች ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብተው ፈጽመዋል የተባለውን ጥቃት አስተባበሉ

በዐማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂዎች፣ ሰሞኑን፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን መንዲዳ ከተማ ገብተው ጥቃት እንደፈጸሙ፣ የአካባቢውን ነዋሪዎች ዋቢ በማድረግ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በመንዲዳ ከተማ፣ በፋኖ ታጣቂዎች እና በክልሉ የጸጥታ አካላት መካከል በነበረው ግጭት፣ ከኦሮሚያ ክልል በኩል ሦስት ሰዎች፣ እንዲሁም ስምንት የፋኖ ታጣቂዎች እንደተገደሉ፣ አንድ እማኝ እና የወረዳው ባለሥልጣን በዘገባው ላይ ገልጸው ነበር፡፡

ለዚኽ ክሥ፣ የፋኖ ታጣቂዎች፣ በዛሬው ዕለት በሰጡን ምላሽ፣ በወቅቱ ወደ ደብረ ብርሃን እየተንቀሳቀስን እያለን ለተፈጸመብን ጥቃት ነው የአጸፋ ምላሽ የሰጠነው፤ ብለዋል፡፡ በግጭቱ፣ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃት እንዳልፈጸሙም ገልጸዋል፡፡

በስፍራው ከተካሔደው ግጭት በኋላ፣ በአብቹ እና ኘዓ ወረዳ የሚኖሩ የዐማራ ተወላጆች፣ በማንነታቸው ብቻ ለእስር እየተዳረጉ እንደሚገኙ፣ የፋኖ ታጣቂዎቹ አመልክተዋል፡፡

የወረዳው የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ አቶ አብደታ ኀይልዬ በሰጡት ምላሽ፣ ከግጭቱ ጋራ ተያይዞ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸው፣ ነገር ግን፣ “ጽንፈኛ” ካሏቸው ታጣቂዎች ጋራ “ሲተባበሩ የነበሩ እንጂ፣ በማንነታቸው የታሰሩ አይደሉም፤” ብለዋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG