በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፋኖ እና በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ግጭት ሰዎች ተገደሉ


በፋኖ እና በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ግጭት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:13 0:00

በፋኖ እና በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ግጭት ሰዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አብቹ እና ኘዓ ወረዳ መንዲዳ ከተማ፣ በኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሰዎች እንደተገደሉ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ።

የወረዳው ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሓላፊ፣ ጥቃቱን ያደረሱት፣ ከመንዲዳ ከተማ 10 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ከሚገኘው ደነባ ከተማ መነሻቸውን ያደረጉ የፋኖ ታጣቂዎች እንደኾኑ ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲገለጽም ኾነ ድምፃቸው እንዲቀረጽ ያልፈለጉና ለጊዜው በአካባቢው እንደሌሉ የተናገሩ አንድ የአካባቢው አመራር፣ ግጭቱ የተፈጠረው፣ የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ወደ ደብረ ብርሃን እያቀኑ የነበሩ የፋኖ ታጣቂዎችን ላለማሳለፍ በመቋቋማቸው እንደኾነ አስረድተዋል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG