በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶኒ፤ አሜሪካና ሰሜን ኮሪያ - ዘ ኢንተርቪው

የሰሞኑ እጅግ የበረታው የዓለም ንግግር ባለፈው ሣምንት ሶኒ ኩባንያን ቀስፎ ይዞት የነበረው የሣይበር ጥቃት ጉዳይ ነበር፡፡

"ዘ ኢንተርቪው" የፊልም ፖስተር
"ዘ ኢንተርቪው" የፊልም ፖስተር

ሶኒ፤ አሜሪካና ሰሜን ኮሪያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሰሞኑ እጅግ የበረታው የዓለም ንግግር ባለፈው ሣምንት ሶኒ ኩባንያን ቀስፎ ይዞት የነበረው የሣይበር ጥቃት ጉዳይ ነበር፡፡

ያንን ጥቃት ያደረሰችው ሰሜን ኮሪያ ነች ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት እየተናገሩ ነው፡፡

የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣናት ያንን ወረራና ጥቃት ለማውጠንጠንና ለመፈፀም ያነሣሣቸው ጉዳይ በመሪያቸው ኪም ዮንግ ኡን ላይ ይሣለቃል የተባለው “ዘ ኢንተርቪው” ተብሎ የተሰየመው ፊልም ለሕዝብ እንዳይታይ ወይም እንዳይወጣ ለማስተጓጎል ነው ተብሏል፡፡

ሰሜን ኮሪያ የጥቃቱን መፈፀም ብትደግፍም እጇ ግን እንደሌለበት ተናግራለች፡፡

በዚህ ሳይበር ጥቃት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውና አሳሳቢ መረጃዎችን የያዙ ሠነዶች እንዲዝረከረኩና እንዲጋለጡ የተደረገ ሲሆን ፊልሙ ካልቆመ በእርምጃቸው እንደሚገፉ “የሰላም ዘቦች” በሚል እራሱን የጠራ የአጥቂዎች ቡድን ዝቷል፡፡

የሳይበር ጥቃት አድራሾቹ በተጨማሪም በቴአትር ቤቶችና በሲኒማ ቤቶች ላይ በአካል አደጋዎችን እንደሚጥሉ በመዛታቸው ሶኒ ኩባንያ የመቶ ሚሊዮን ዶላር ኪሣራ ይደርስብኛል እያለም ቢሆን “ዘ ኢንተርቪው”ን ላለማውጣት ወስኗል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ የጥቃቱን አቀናባሪዎች ፈፃሚዎች እንደምትፋረድ ዝታለች፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG