በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት የመሪዎች ጉባዔ በዋሽንግተን


75ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት ልዩ ዝግጅት
75ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን በማስመልከት ልዩ ዝግጅት

በዋሽንግተን የታደሙት የሰሜን አትላንቲክ ሀገሮች ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል ሀገሮች መሪዎች ሕብረቱ ለዩክሬይን የሚሰጠውን ድጋፍ ለማጠናከር እና የራሳቸውንም የመከላከያ አቅም ለማጎልበት ያለሙትን ጉባዔ ቀጥለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ በበታች ባለሥልጣናት ደረጃ ለወራት ውይይት ሲካሄድበት ከርሟል፡፡ ቀደም ብሎም በዚህ እአአ 2024 መጀመሪያ የአባል ሀገራቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የተወያዩበት ቢሆንም የመጨረሻውን ስምምነት መቋጨት የመሪዎቹ ኅላፊነት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የዛሬው ጉባዔ ውሎ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በኋይት ሐውስ ለመሪዎቹ በሚያደርጉት የዕራት ግብዣ ይጠናቀቃል፡፡

የቃል ኪዳን ድርጅቱ ሰባ አምስት ዓመታት ባስቆጠረው ታሪኩ ያልታየ ሊባል የሚችል ፈተና በተደቀነበት በአሁኑ ወቅት ፕሬዚደንት ባይደን ሰላምን በጥንካሬ አማካይነት ዕውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሚያስገነዝብ ጠንካራ ንግግር አድርገዋል፡፡

ባይደን ለሦስት ቀናት የሚዘልቀውን ጉባዔ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር “ከምንጊዜውም ይበልጥ ጠንካራ መሆናችን ጥሩ ነው ምክንያቱም ይህ የታሪክ ወቅት በአንድነት ጠንክረን እንድንገኝ የሚጠይቅ ነውና” ብለዋል፡፡

“አምባገነኖች ሰማኒያ ዓመታት ያስቆጠረውን ዓለምአቀፍ ሥርዓት ሊቀለብሱ ይፈልጋሉ፡፡ ሽብርተኛ ቡድኖች ብጥብጥ የሚቀሰቅሱ እና ሰዎችን ለስቃይ የሚዳርጉ የተንኮል ሴራዎች መሸረባቸውን ቀጥለዋል፡፡ በአውሮፓ የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን ዩክሬይንን ወርረው የከፈቱባትን ጦርነት ቀጥለዋል” ብለዋል፡፡

ባይደን አስከትለውም “ፑቲን የሚፈልጉት ዩክሬይንን ሙሉ በሙሉ ማንበርከክ ዲሞክራሲዋን መደምሰስ፡ ባሕሏን እና ራሷን ከዓለም ካርታ ላይ ማጥፋት ነው” ያሉት ባይደን “ፑቲን ከዚያ ያነሰ የሚፈልጉት ነገር የለም፡፡ ፑቲን ዩክሬይን ላይ እንደማያቆሙም እናውቃለን፡፡ ነገር ግን እንዳትሳሳቱ ዩክሬይን ፑቲንን ማስቆም ትችላለች፡፡ ታስቆማቸዋለችም” ብለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG