በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለዩክሬን የሚሰጠው ድጋፍ ትኩረት የሚያገኝበት የኔቶ የዋሽንግተን ጉባኤ ተጀመረ


ዋሽንግተን ኮንቬንሽን ሴንተር
ዋሽንግተን ኮንቬንሽን ሴንተር

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት - ኔቶ ጉባኤ ዛሬ በዋሽንግተን ሲከፈት፤ በሩስያ የተፈጸመባትን ወረራ ለመከላከል በያዘችው ወታደራዊ ዘመቻ ዩክሬይን መደገፍ ዋናው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ተገለጠ። የዩክሬንን ጦር ለመርዳት አሁን አገራት በተናጠል ያደርጓቸው የነበሩትን ጥረቶች፤ የኔቶ መሪዎች ‘በኔቶ ወደተቀናጀ መርሃ ግብር ለመውሰድ የተያዘውን እቅድ ያጠናቅቃሉ’ ተብሎ ይጠበቃል።

ለዩክሬይን የሚሰጠው ይህ እርዳታ የዩክሬን መሪዎች ከሚደርስባቸው የአየር ጥቃት ለመከላከል እና ብሎም የሩስያን ጦር ግስጋሴ ለመመከት የሚያስፈልጓቸውን፤ በተደጋጋሚ የጠየቋቸውን አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች፣ የአየር መከላከያ እና ሌሎች እርዳታዎች የሚጨምር መሆኑም ተመልክቷል። ጉባኤው በተጨማሪም ዩክሬንን ወደ ኔቶ አባልነት የሚወስደውን መንገድ ያጤናልም ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬው አጀንዳ አበተጨማሪም በዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን የሚመሩት በሴቶች፣ በሰላም እና በደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይታ ያካትታል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የኔቶን 75ተኛ አመት የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ዛሬ ማምሻው ላይ በሚካሄደው የመታሰቢያ ዝግጅት ወቅት ንግግር ያሰማሉ።

ባይደን ወደ ጉባኤው አዳራሽ የሚያቀኑት ታዲያ፤ ባለፈው የሰኔ ወር አጋማሽ ከሪፐብሊካኑ ዕጩ ተፎካካሪያቸው ትራምፕ ጋር ክርክር ባደረጉበት ወቅት ያሳዩት ደካማ አፈጻጸም በአገር ውስጥ የእድሜያቸውን መግፋት አስመልክቶ የሚነሱትን ስጋቶች በቀሰቀሰበት እና በዳግም የምርጫ ዘመቻው ዙሪያ ጥያቄዎች እየተነሱ ባሉበት ወቅት ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG