በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋስ እንዲፈቱ ተወስኖ የነበረው እነ ናትናኔል ፈለቀ ይግባኝ ተጠየቀባቸው (ጠበቃውን አነጋግረናል)


ናትናኔል ፈለቀ
ናትናኔል ፈለቀ

ቀደም ሲል በእስር ላይ ቆይተው ከተለቀቁት የዞን ዘጠኝ የኢንተርኔት አምደኞች አንዱ የሆነው ናትናኔል ፈለቀ እንዲሁም ጸደቀ ድጋፌ እና አዲስ አለም ደስታ ዛሬ በዋስ እንዲፈቱ ፍርድቤት ቢወስንም ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ይግባኝ በመጠየቁ ለነገ ተቀጥሯል።

የናትናኤል ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን በዛሬው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፤ ተጠርጣሪዎቹና ጠበቃው ተጠርጣሪዎቹን በተጠረጠሩበት “ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው ላሊበላ ሬስቶራንት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በአካባቢው የነበሩ ሰዎች እንዲሰሟቸው በማድረግ በቢሾፍቱ የኢሬቻ አክባሪዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ትክክል እንዳልሆነ በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ለተቃውሞ እንዲነሳሱ በሚያደርግ መልኩ ሲያወሩ ነበር” በሚል ምክንያት አስሮ ለማስቀመጥ የሚያስችል ምንም ምክንያት እንደሌለው በመግለጽ ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ ተጠርጣሪዎቹ አልሰጡም የተባለውን የጣት አሻራ እንዲሰጡና ነገ መስከረም 27 ቀን 2009 ዓ.ም 5ሺሕ ብር የሚበቃ ዋስ በማስያዝ እንዲፈቱ በተጨማሪም ተለዋጭ ትዕዛዝ እስከሚሰጥ ድረስ ከአገር ውስጥ እንዳይወጡ ተወስኖ የነበረ ቢሆንም ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ በማለቱ ይግባኝ በመጠየቁ ለነገ ተቀጥሯል።

የናትናኤል ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን ከጽዮን ግርማ ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርገዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

በዋስ እንዲፈቱ ተወስኖ የነበረው እነ ናትናኔል ፈለቀ ይግባኝ ተጠየቀባቸው (ጠበቃውን አነጋግረናል)
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

XS
SM
MD
LG