በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፌደራሉ እና በትግራይ ክልል መካከል አሁንም ያለመተማመን አለ - ጌታቸው ረዳ


በፌደራሉ እና በትግራይ ክልል መካከል አሁንም ያለመተማመን አለ - ጌታቸው ረዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

በፌደራሉ እና በትግራይ ክልል መካከል አሁንም ያለመተማመን አለ - ጌታቸው ረዳ

በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በትግራይ ክልል መካከል አሁንም አለመተማመን እንደሚታይ፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ገለጹ።

አቶ ጌታቸው ትላንት ለክልሉ የብዙኀን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፤ በፌደራል መንግሥቱ በኩል፣ የክልሉ አመራሮች የሰላም ስምምነቱን እንደ ጊዜ መግዣ እየተጠቀሙበት ነው፤ የሚል አመለካከት እንዳለ ጠቅሰዋል።

በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር በኩል ደግሞ፣ የፌደራሉ መንግሥት የክልሉን አመራሮች አንድነት ለመናድ ይንቀሳቀሳል፤ የሚል አስተሳሰብ እንዳለ ተናግረዋል።ይህንን አለመተማመን ለመቅረፍም ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ተናግረዋል።

የህወሓት ሕጋዊ እውቅና እንዲመለስ በፌደራሉ መንግሥት እና በክልሉ አመራሮች መካከል ከመግባባት ላይ እንደተደረሰ የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፣ በቀጣይ ሳምንት ደግሞ አደራዳሪዎች በተገኙበት የፕሪቶርያው ስምምነት አፈጻጸም እንደሚገመገም አስታውቀዋል፡፡

አቶ ጌታቸው መግለጫውን የሰጡት፣ ከህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋራ በተገኙበት፣ ሰሞኑን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያካሔዱትን ግምገማ ተከትሎ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሩት ይኸው ግምገማ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ በድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ እና በሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ላይ ያተኮረ እንደኾነ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG