በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የትግራይ ክልል አመራሮች ለግምገማ ተቀምጠዋል


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የትግራይ ክልል አመራሮች፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የትግራይ ክልል አመራሮች፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ከተቋቋመበት ጊዜ አንሥቶ የነበሩትን ሥራዎች እና መሻሻሎች በጥልቀት መገምገም መጀመራቸውን ጽ/ቤታቸው አስታውቋል።

የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም እና የድኅረ ግጭት መልሶ ግንባታ የግምገማው ትኩረት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አመልክቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተካሔደ ባለው የግምገማ መድረክ፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ እና ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋራ ገጽ ለገጽ የተገናኙት የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል፣ እንዲሁም ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ ኃላፊዎች እየተሳተፉ መሆናቸውን በገፁ ላይ በምስል ተጋርቷል።

በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት የፌደራሉ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር በርካታ ድሎችን አስመዝግበዋል"

ባለፈው ሰኞ፣ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ በሰጡበት ወቅት፣ "በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት የፌደራሉ መንግሥት እና የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በትብብር በርካታ ድሎችን አስመዝግበዋል" ሲሉ ከስምምነቱ በኋላ ጥገና የተደረገላቸውንና አገልግሎት የጀመሩ የመሠረተ ልማት ተቋማትን ዘርዝረዋል፡፡ ቀሪ ሥራዎችም እንዳሉ ጠቁመው፣ በትብብር እና በውይይት መፈጸም እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG