በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውይይት ተደረገ


በትግራይ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውይይት ተደረገ
በትግራይ ጉዳይ ዓለምአቀፍ ውይይት ተደረገ

"የሰላም ግንባታና ፍትሕ በድህረ-ጦርነት ትግራይ” በሚል ፍሬ-ሃሳብ ከትናንት በስተያ ቅዳሜ፣ ጥር 18 / 2016 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በኢንተርኔት ተካሂዷል።

ምሁራንና የማኅበራት ተወካዮች የጥናት ፅሑፎች ባቀረቡበት መድረክ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳና የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሃመር ተናግረዋል።

ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም. ፕሪቶሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ የተፈረመውን ፀብ የማቆም ስምምነት እንደተፈለገው ሙሉ በሙሉ ፈጥኖ ተፈፃሚ አለመደረጉን አምባሳደር ሃመር አስታውሰው ትግራይ ውስጥ የተኩስ ድምፅ እንዲቆምና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲቀንስ ሁለቱም ወገኖች ‘አድርገዋል’ ላሉት ጥረት አመስግነዋል።

በፍትሕና በተጠያቂነት ዙሪያ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ንግግሮች እንዲካሄዱ ዩናይትድ ስቴትስ በጥረቷ እንደምትቀጥል፣ ‘ትግራይ አሉ’ የሚባሉ የኤርትራ ወታደሮች ስለሚወጡበት ሁኔታና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሃመር ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ስምምነቱ ከተፈረመ ከ14 ወራት በላይ ማስቆጠሩን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳ ጠቁመው አሁንም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ አሳስበዋል። አቶ ጌታቸው አክለው “የትግራይ ህገ-መንግሥታዊ ግዛት ወደነበረበት አልተመለሰም” ማለታቸውን ባልደረባችን ገብረ ገብረመድህን ዘግቧል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG