ዋሺንግተን ዲሲ —
ኬንያውያን ዛሬ በሃገሪቱ ለሁለተኛ ጊዜ እንደገና በተካሄድው ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ድምጽ ሰጥተዋል። ዛሬ ድምፅ ለመስጠት የወጣው ሕዝብ ቁጥር ነሐሴ 1 ቀን 2010 ዓም በተካሄደው በመጀመሪያው ምርጫ ከወጣው ያነሰ ቢሆንም ባንዳንድ የተቃዋሚው ፓርቲ ጠንካራ አካባቢዎች ግጭቶች መፈጠራቸውም ተዘግቧል።
በበርካታ የድምፅ መስጪያ አካባቢዎች የፀጥታው ጉዳይ አስተማማኝ ባለመሆኑም እስከ ነገ በስቲያ እንዲራዘም ተደርጓል።.
የኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንታዊው ምርጫ ዳግም እንዲካሄድ ያዘዘው፣ የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ውጤቶቹን ሲያሰራጭ ስህተት ፈፅሟል ሲል በመክሰስ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ጂል ክሬግ ከናይሮቢ ዘግባለች፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ