በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ዳኢሽ ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ ይመታል” - የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አል አባዲ


“ሞሱልን ነጻ ልናወጣ መምጣታችን ነው።" የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አል አባዲ

የኢራቅ ጠቅላይ ሚንስትር ሃይደር አል አባዲ የመንግሥታቸው ሓይሎች ራሱን የእስልምና መንግሥት ብሎ ከሚጠራው ጽንፈኛ ቡድን ነጥቀው የተቆጣጥሩዋትን ቁልፍ ከተማ ራማዲን ዛሬ ጎብኝተዋል።

የኢራቅ መንግሥት ቴለቭዢን ሚስተር አባዲ ራማዲ መጓዛቸውን ከመግለጽ በስተቀር ሌላ ዝርዝር አልተናገረም። አንድ የኢራቅ ወታደራዊ መኮንን ለአሶሲየትድ ፕሬስ እንደተናጋሩት ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአካባቢው የጸጥታና የአስተዳደር ባለስልጣናት ጋራ ተወያይተዋል።

ዛሬ የኢራቅ ሓይሎች የእስልምና መንግሥት ተዋጊዎችን ከከተማዋ ሲመነጥሩ በየመንገዱ እና በህንጻው የተጠመዱ ቦምቦችን ሲያመክኑ ውለዋል። በከተማዋ ዳር ዳሩን ኣልፎ ኣልፎ ተኩስ እንደነበር ተዘግቧል።

ሞሱልን ነጻ ልናወጣ መምጣታችን ነው። ዳኢሽ ለመጨረሻ ጊዜ ድባቅ ይመታል።
የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር አል አባዲ

ባለፈው ግንቦት ራማዲ የእስልምና መንግሥት ቡድን እጅ መውደቋ ጽንፈኛውን ቡድን ለመመከት ሲሟሟቱ ለነበሩት ለጠቅላይ ሚኒስትር አባዲ መንግሥት እና ለጦር ሰራዊቱ ከባድ ምት እንደነበር አይዘነጋም።

ትናንት ጦር ሰራዊቱ ከተማዋን መልሶ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ታዲያ አባዲ በቴሌቭሺን ባደረጉት ንግግር መጪው የአውሮፓውያን 2016 ዓ.ም. የእስልምና መንግሥት ከኢራቅ የሚወገድበት ዓመት ይሆናል ሲሉ አውጀዋል። ቀጣይ ዒላማችን ደግሞ ሁለተኛዋ የኢራቅ ትልቋ ከተማ ደግሞ ትሆናለች ብለዋል።

XS
SM
MD
LG